ቸኪያ

ከውክፔዲያ

Česká republika, Česko
ቼክ ሪፐብሊክ

የቼክ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ የቼክ ሪፐብሊክ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Kde domov můj

የቼክ ሪፐብሊክመገኛ
የቼክ ሪፐብሊክመገኛ
ዋና ከተማ ፕራግ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ቼክኛ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ
ሚሎስ ዜማን
ፔትር ፊያላ
ዋና ቀናት
ታኅሣሥ 23 ቀን 1985
 
የነፃነት ቀን
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
78,866 (115ኛ)
2
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
10,553,948 (84ኛ)
ገንዘብ ቼክ ኮሩና
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +420
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .cz

የቸክ ሪፐብሊክ (ወይም በአጭሩ ቸኪያ) በመሀከላዊ የአውሮፓ ክፍል የምትገኝ ሀገር ናት። ቸክ 78,871 ስኩዌር ኪሎሜትር የሚያክል ኮረብታማ ሀገር ስትሆን፣ የወቅያኖስ ወይም የምድር አየር ፀባይ አይነት አላት። ፕራጉ ዋና ከተማዋ ሲሆን ብርኖ እና ኦስትሮቫ ታላላቅ ከተሞቿ ናቸው። በሚያዝያ 8 ቀን፣ 2008 ዓም የ«ቼክ ረፑብሊክ» አጭር ስም በይፋ «ቸኪያ» ሆነ።

ቸክ የ200 አመት ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን እስከ 1806 ዓም በቅዱስ ሮማ ግዛትና እስከ 1918 ዓም በሃብስበርግ ስርወ መንግስት ትመራ ነበር። ከዛም በኋላ ቼክእስሎቫኪያ መመስረትን ይከተላል። በሁለተኛው የአለም ጦርነት የቼክ መሬት በጀርመን ቁጥጥር ስር ስትውል በ1948 ዓም ደግሞ ቼክ የሶቬትን ክልል ተቀላቀለች። በ1989 ዓም በተረገው የቬልቬት አብዮት የኮሚኒስት አገዛዝ እንዲያበቃ ሲያደርግ በጥር 1 1993 ዓም የቸክስሎቫክያ ግዛት ለሁለት ተከፈለች፣ ቼክና ስሎቫክያ እንደ አንድ ሀገር መሆን ጀመሩ።

ቼክ ያደገች ሀገር ናት። ቼክ በአውሮፓ አህጉር አለች የተባለች የኢአማኝ ሀገር ናት። በፒው ምርምር ጥናት መሰረት ከ60% በላይ የሚሆኑ የቸክ ህዝቦች ኢ-አማኝ እንደሆኑ አረጋግጧል። ይህም በአንፃሩ ከአውሮፓ ሀገራት እጅግ ይበልጥ ናቸው። ቸካውያን የሊበርታሪያን አስተሳሰብ አላቸው። ማለትም ጣልቃ ገብነትና የሀያላን ተፅዕኖዎችን የምትቃወም፣ እኩልነት የምትሻ ሀገር ነት። ቸካውያን ልክ እንደ ስካንዲኒቭያን ሀገራት ሁሉ፣ የሀይማኖት ህልውና መኖርን የሚቃወሙና የግለሰብ ነፃነትን፣ የግብረሰዶም መብት፣ ውርጃ፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ወሲባዊ ነፃነትን በሚደግፉ ናቸው። ዋናው የሚለያዩበት ነገር ቸክ ሪፐብሊክ ውስጥ የሰይጣን እምነት ስለሌላት ነው። ይህም በተለየ ሁኔታ ቸክ ሴኪውላር ሀገር ናት። ነገር ግን የምዕራብያውያን አሰተሳቦችና ርዕዮተ ዓለም አስፈላጊ ነው ብላ የተቀላቀለች ፀረ-ኮሚኒስት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰአትም በሩሶ-ዩክሬን ጦርነት አማካኝነት ለምዕራብያውያን ወግና ሩሲያን የምትፋለም ሀገር ናት።