ለንደን

ከውክፔዲያ
(ከሎንዶን የተዛወረ)
Jump to navigation Jump to search

ለንደንዩናይትድ ኪንግደም ዋና ከተማ ነው።

ቢሾፕጌት የሚሰኘው በር

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 7,615,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 7,429,200 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 51°30′ ሰሜን ኬክሮስ እና 00°10′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ለንደን «ሎንዲኒዩም» ተብሎ ምናልባት 39 ዓ.ም. ግድም ተመሠረተ። በ92 ዓ.ም. የሮሜ መንግሥት ክፍላገር መቀመጫ ከኮልቸስተር (ካሙሎዱኑም) ወደ ሎንዲኒዩም ተዛወረ፤ ሮማውያንም እስከ ወጡ እስከ 402 ዓ.ም. ድረስ እንዲህ አገለገላቸው። አንግሎ-ሳክሶኖች ከዚያ ገብተው ሉንደንዊክ የሚባል መንደር በ600 ዓም. ግድም በዚያ ሠፈሩ። በ1058 ዓ.ም. ከዊንቸስተር ጋር የእንግላንድ ዋና ከተማ ሆነ፤ በ1098 ዓ.ም. የእንግላንድ ብቸኛ ዋና ከተማ ሆነ።

Commons-logo.svg
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ለንደን የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።