Jump to content

ኪዳነ ወልድ ክፍሌ

ከውክፔዲያ

አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ (ከ፲፰፻፷፬ እስከ ፲፱፻፴፯ ዓ.ም.)

የሕይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በሸዋ ክፍለ ሀገር በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በ፲፰፻፷፬ ዓ.ም. ተወለዱ። ለትምህርት ሲደርሱ በአካባቢያቸው የነበረውን የአገራቸውን ትምህርት ተማሩ። በኋላም ወደ ጎንደር ተጉዘው የመጻሕፍትን ትርጓሜ አጠኑ። በጊዜው የነበራቸው የቀለም አቀባበል፣ የሚስጥር መመራመርና መራቀቅ በጉባኤው ላይ «የቀለም ቀንድ» የሚል ቅጽል ተሰጣቸው።[1]ማናቸው ማናቸው

አለቃ ኪዳነወልድ ከግዕዝአማርኛ ሌላ ዐረብኛዕብራይስጥላቲን፣ ሌሎችንም ቋንቋዎች አጠናቅቀው ያውቁ ነበር ። አለቃ ኪዳነወልድ በእየሩሳሌም ለ፳፪ ዓመት ተቀምጠዋል ። በዚህም ወቅት ብሉይና ሐዲስ በሦስት ቋንቋ ጠንቅቀው አመሳክረው ተርጕመዋል ። ኪዳነወልድ ክፍሌ በ፲፱፻፳፮ ዓ.ም. የመጀመሪያውን መዝገበ ፊደል አውጥተው ከልዩልዩ ቋንቋዎች ጋር በማመሳከር አሳትመዋል ። የኢትዮጵያ ፊደል አመጣጡንና ባህሉን በውል አስተባብረው በማቅረባቸውም በጊዜው ተቋቁመው ለነበሩት ትምህርት ቤቶች መመሪያና መማሪያ ለመሆን በቅተዋል ። ቀጥለውም ትንሽ አማርኛ ፊደል ከአረብና ከዕብራይስጥ አቆራኝተው አሳትመዋል ።[1]

አለቃ ኪዳነወልድ በተለያየ ዘይቤ ያቀርቧቸው የነበሩት ግጥሞች ለትውልድ ታላቅ ጥቅም ይሰጣሉ ተብለው የሚገመቱ ናቸው ። እንዲያውም ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪቃ የብዙ ሺሕ ዘመናት ነጻ አገር ባለፊደልና ባለቋንቋ የሆነች እሷ ብቻ ስለሆነች ትውልድ ያገሩን ትምህርት በመጀመሪያ እንዲማር ያካሂዱት የነበረው ቅስቀሳ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ። በዓለም ስማቸው የገነነ የሥነ ጥበብ፣ የኪነ ጥበብ ፣ የጽሑፍ ባለአጉዛዎች የሚደነቁባቸው በራሳቸው ቋንቋ ጽፈው ለዓለም የአቀረቧቸው ሥራዎች ናቸው ይላሉ ።[1]

አለቃ ኪዳነወልድ ለኢትዮጵያ ባላቸው ዐቅም በብሔራዊ ስሜት ተነሳስተው ለታሪክ የሚቀርቡ በርከት ያሉ መጻሕፍት ጽፈው አሳትመዋል ። በተለይም ከዘጠኝ መቶ ገጾች በላይ የሆነው «የሰዋሰው መጽሐፍ» ታላቅ እንደሆነ ይነገራል ። አለቃ ኪዳነወልድ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታላቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሰው ነበሩ ።[1]

አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በተወለዱ በ ፸፪ ዓመታቸው ፤ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፮ ዓመተ ምሕረት ዐርፈው ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።[2]

  1. ^ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲብሔራዊ ቢብሎግራፊ (የደራሲያን አጭር የሕይወት ታሪክ) ፤ ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. [1] Archived ጁላይ 20, 2011 at the Wayback Machine (ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. የተነበበ)