ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ

ከውክፔዲያ
(ከዘርአ ያዕቆብ የተዛወረ)
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ
ዘርአያዕቆብ ከመብዓ ጽዮን ድርሰት.JPG
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ1434 እስከ 1468 እ.ኤ.አ.
ቀዳሚ ዓምደ ኢየሱስ
ተከታይ በእደ ማርያም
ባለቤት ንግሥት እሌኒ
ሙሉ ስም ቆስጠንጥንዮስ (የዘውድ ስም)
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ቀዳማዊ ዳዊት
እናት ንግሥት ክብረ እግዚ
የተወለዱት 1399 እ.ኤ.አ. በትልቅ መንደር፣ ፈተገር ክ/ሀገር
የተቀበሩት ደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ክርስትና


የጥንቱ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት

አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስትክብረ እግዚ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው።

አስተዳደር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዘራአ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው።

ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። ንግስት እሌኒሀድያ ንጉስ ልጅ ስትሆን በህጻንነቱዋ የእስልምና ተከታይ የነበረች ቢሆንም በጋብቻው ወቅት ክርስቲያን ሆናለች።

በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤ/ክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴን ትምህርት የተቀበሉ በወንጌል ትምህርት የጸኑ ሰዎች ገዳም ሲሆን በአዲስ ኪዳን እንደተጻፈው በክርስቶስ ማመን እንጂ ለመስቀል መስገድና ለስእል መስገድ ለንጉሥም እንደ መለኮት መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ። በማለታቸውም አፍንጫቸውና ምላሳቸው እየተቆረጠ፣ የከብት አጎዳ እየተነዳባቸው የተገደሉት ብዙ ናቸው። አስተማሪያቸው እስጢፋኖስም ተሰቃይቶ ተገድሎአል።

በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር።

በ1456 ዓ.ም የሀሌይ ኮሜት (ባለ ጭራ ኮኮብ) ደማቅ ብርሃኑዋን እያፈናጠቀች ስታልፍ፣ አጼው የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል። እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።

ድርሰቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ 3 መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው። እነሱም መጽሃፈ ብርሃንጦማረ ሃይማኖትመጽሃፈ ምላድመጽሃፈ ስላሴ ይሰኛሉ። እነዚህ መጽሐፎች ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ሆነው በዘመናቸው የተነሱትን ለመስቀልና ለስእልመስገድ የተገባ አይደለም የሚሉትን ደቀ እስጢፋ የተባሉትን ክርስቲያኖች ለማውገዝ ያገለገሉም ናቸው።

በተረፈ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መባዓ ጽዮን የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጻዲቅ የኖረው በኒሁ ንጉስ ዘመን ነበር። ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ከኢትዮጵያ ነገሥታት 265ተኛ ነበሩ። [1]

ማጣቀሻወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • (እንግሊዝኛ) David Buxon, The Abyssinians (New York: Praeger, 1970), pp. 48f
  • (እንግሊዝኛ) Richard K. P. Pankhurst, The Ethiopian Royal Chronicles (Addis Ababa: Oxford University Press, 1967), p. 32f.
  • (እንግሊዝኛ) Richard Pankhurst, The Ethiopians: A History (Oxford: Blackwell, 2001), p. 85.
  • Edward Ullendorff, however, attributes only the Mahsafa Berha and Mahsafa Milad.</ref>

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]