ይማም

ከውክፔዲያ

ራስ ይማምኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት1817 እስከ 1820 ዓም ድረስ የበጌምድር ራስ፣ የየጁ ስርወ መንግስት እንደራሴ ነበሩ። የራስ ጉግሣ ልጅ ነበሩ።

አባታቸው ራስ ጉግሣ በ1817 ዓም ዐርፈው ይማም እንደራሴ በሆኑበት ወቅት ወንድማቸው ማርዬ ወዲያው ዐመጹባቸው።[1]

በጸሐፊው አቶ ትሪሚንግሃም ዘንድ፣ ራስ ይማም ለተዋሕዶ እምነት ሳይሆን ለእስልምና ድጋፋቸውን በገሐድ ሰጡ።[2] ከዚህም በላይ አቡነ 3ኛ ቅሪሎስሦስት ልደት ክርክር ውስጥ በዕርቅ ሲገቡ፣ ራስ ይማም ተናድደውባቸው ቅሪሎስን ወደ ሐይቅ ሐይቅ ገዳም በግዞት ሰደዱዋቸው።[3]

ራስ ይማም በጎጃም በደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ ላይ እየዘመቱ፣ ደጃዝማች ሃይለ ማርያም ከስሜን ግዛት ገሥግሠው ወደ ጎንደር ደርሰው ንጉሠ ነገሥቱን ዓፄ ጊጋርን ገልብጠው በምትካቸው ዓፄ 3ኛ ባዕደ ማርያም አስነሡ። ራስ ይማም ይህን በሰሙበት ጊዜ፣ በድንግል በር በኩል ተመልሰው ደጃች ሃይለ ማርያምን እስከ ዋልደባ ድረስ አባረሩት። በዚያ ሥፍራ ለሦስት ቀን ከታገሉ በኋላ ደጃች ሃይለ በወገራ በኩል ወደ ስሜን ግዛት ሸሽተው ዓረፉ። ይህም ስለሆነ ራስ ይማም አጼ ጊጋርን ወደ ዙፋናቸው ሊመልሷቸው ቻሉ።[4]

ጸሐፊው አቶ ስቨን ሩበንሶን እንደ ገለፀው፣ የደጃች ሃይለ ማርያም ልጅ ውቤ ሃይለ ማርያም በውግያው ተማረከ፣ የይማም ወዳጅ ደጃች ሜሩ ዘደምቢያ ግን ልጁን ነጻ እንዲያውጡት አሳመኑዋቸው። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ውቤ ደጃች ሆነው ከራስ ይማም ጋር ተባብረው ደጃች ጎሹንና ደጃች ሜሩን በኮሶበር ውጊያ በ1820 ዓም አሸነፏቸው። ጎሹ ወደ ጎጃም እየሸሹ፣ ሜሩ ከውግያው ቀጥሎ በወታደር ተገደለ።[5] በኋላ ራስ ይማም በደብረ ታቦር በግፍ ሞቱ።[4]ታቦር እየሱስ ቤተክርስቲያን ተቀብረዋል።[6]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Donald Crummey, "Family and Property amongst the Amhara Nobility", Journal of African History, special issue: The History of the Family in Africa, 24 1983, p. 218መለጠፊያ:Closed access
  2. ^ J. Spencer Trimingham, Islam in Ethiopia (Oxford: Geoffrey Cumberlege for the University Press, 1952), p. 111
  3. ^ Mordechai Abir, Ethiopia: The Era of the Princes; The Challenge of Islam and the Re-unification of the Christian Empire (1769-1855) (London: Longmans, 1968), p. 42 and note 2.
  4. ^ H. Weld Blundell, The Royal chronicle of Abyssinia, 1769-1840 (Cambridge: University Press, 1922), p. 485
  5. ^ Sven Rubenson, King of Kings: Tewodros of Ethiopia (Addis Ababa: Haile Selassie I University, 1966),pp. 19f
  6. ^ Pankhurst, Richard K. P. (1982). History of Ethiopian Towns. Wiesbaden: Franz Steiner Verlag. p. 266. 
ቀዳሚው
ጉግሣ
የጁ ስርወ መንግስት
1817-1820 ዓም
ተከታይ
ማርዬ