Jump to content

ንዋየ ክርስቶስ

ከውክፔዲያ

==

ዓፄ ንዋየ ክርስቶስ
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ1344 እስከ 1372 እ.ኤ.አ.
ቀዳሚ ቀዳማዊ ዓፄ አምደ ጽዮን
ተከታይ ዓፄ ንዋየ ማርያም
ልጆች ዓፄ ንዋየ ማርያም
ዓፄ ዳዊት ፩ኛ
ሙሉ ስም ሰይፈ አርድ (የዙፋን ስም)
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ዓፄ አምደ ጽዮን
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

==


ዓፄ ንዋየ ክርስቶስ በዙፋን ስማቸው "ሰይፈ አርድ" ከ1344 - 1372 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ነበሩ። የቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን የመጀመሪያ ልጅ ነበር። በዚህ ንጉስ ዘመን አሊ ኢብን ሳብር አድ ዲን የተባለ የወላሽማ ስረወ መንግስት በማመጹ ንጉሱ በይፋት እና አዳል ዘመቻ አደረገ። በዚህ ዘመቻ መሪውና ልጆቹ ስለተማርኩ የይፋት ሱልጣኔት በታሪክ አበቃለት። ንጉሱ ሁሉን ለእስር ቢዳርጉም የመሪውን ልጅ አህመድን ግን የይፋት አስተዳዳሪ አድርገው ሾሙት። ይህ በዚህ ቆይቶ ከ8 አመት በኋላ አሊ-አዲን ከእስር ተፈቶ ልጁ ከስልጣን ወርዶ እርሱ እንደገና መሪ ሆነ። በልጅና በአባት ከፍተኛ ጥል ስለነበር በንጉሱ አማላጅነት ነበር ለልጁ ትንሽ ክ/ሃገር በአስተዳዳሪነት የተሰጠው። [1]

የግብጽ ዘመቻ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ንዋየ ክርስቶስ በታሪክ በተለይ የሚጠቀስበት የግብጽ ቤ/ክርስቲያን ጠባቂ (protectorate) በመሆን ነው። የግብጽ ሱልጣን የነበረው አል ሳሌህ አሌክሳንድሪያውን ጳጳስ ማርቆስ ፬ኛ ባሰረበት ወቅት በኢትዮጵያ የነበሩ ግብጻዊ ነጋዴወችን ካሰረ በኋላ ሙሉ ሰራዊቱን በማስነሳት በግብጽ ላይ ዘመተ። በዚህ ጊዜ ፓትሪያርኩ ክእስር ሲፈቱ ንጉሱም በዚህ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከግብጹ ሱልጣን መልዕክተኞች ደረሱት[2] ንጉሱ ወደ አገራችው ቢመለሱም የሱልጣኑን መልዕክተኞች ግን በዕስር አብረው ይዘው ነበር። [3]

ከዚህ በተረፈ አጼ ስይፈ አርድ በአሁኑ ደቡብ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር ፣ በርሳቸው ዘመን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ የታቦር እየሱስ እንደታነጸ ታሪክ ያትታል [4]። በወሎ ሃይቅ እንዲሁ ጥንታዊ የነበረውን ደብረ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን መልሰው በማነጽ ሲታወቁ ይህ ቤ./ክርስቲያን በአህመድ ግራኝ 1531 ተዘርፎ ተቃጥሏል። እስካሁን በሚገኙ የመሬት ስሪት መዝገቦች መሰረት የዚህ ንጉስ ግዛት ቢያንስ ቢያንስ እስከ ሰራየ፣ የአሁኑ ኤርትራ ድረስ ይደርስ ነበር። [5]


  1. ^ Taddesse Tamrat, Church and State, pp 146-8; E.A. Wallis Budge, A History of Ethiopia: Nubia and Abyssinia, 1928 (Oosterhout, the Netherlands: Anthropological Publications, 1970), p. 299.
  2. ^ Taddesse Tamrat, Church and State, pp. 253f; Paul E. Henze, Layers of Time: A History of Ethiopia (New York: Palgrave, 2000), p. 67
  3. ^ Sihab ad-Din Ahmad bin 'Abd al-Qader, Futuh al-Habasa: The conquest of Ethiopia, translated by Paul Lester Stenhouse with annotations by Richard Pankhurst (Hollywood: Tsehai, 2003), p. 265.
  4. ^ Éthiopie By Luigi Cantamessa, Marc Aubert ገጽ 181
  5. ^ G.W.B. Huntingford, The Historical Geography of Ethiopia (London: The British Academy, 1989), p. 82