Jump to content

ፊሊፒንስ

ከውክፔዲያ
(ከፊልፒንስ የተዛወረ)

ፊሊፒንስ ሪፐብሊክ
Republika ng Pilipinas

የፊሊፒንስ ሰንደቅ ዓላማ የፊሊፒንስ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Lupang Hinirang

የፊሊፒንስመገኛ
የፊሊፒንስመገኛ
ዋና ከተማ ማኒላ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፊሊፒንኛ
እንግሊዝኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
 
ሮድሪጎ ዱቴርቴ
ሌኒ ሮብሬዶ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
300,000 (72ኛ)
0.61
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
100,981,437 (12ኛ)
ገንዘብ ፊሊፒንስ ፔሶ (₱)
ሰዓት ክልል UTC +8
የስልክ መግቢያ 63
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .ph


ፊሊፒንስእስያ ያለ ደሴት አገር ነው። ዋና ከተማው ማኒላ ነው።

ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችና ብሔሮች በፊሊፒንስ ይገኛሉ። ዋና መደበኛው ቋንቋ ፊሊፒንኛተጋሎግኛ ይፋዊ አይነት ነው። ከባህሎቹ ልዩነት የተነሣ፥ በደሴቶቹ ላይ ብዙ ልማዳዊ የሙዚቃ አይነቶች አሉ። ከነዚህ ልዩ ልዩ ሙዚቃዊ ፈሊጦች ጋራ በፊሊፒኖ ባህል የተለያዩ ልማዳዊ ጭፈራ አይነቶች ይሄዳሉ። ለምሳሌ ቲኒክሊንግካሪኖሳ እና ሲንግኪል የተባሉ ጭፍራዎች አሉ። በፊሊፒንስ አንዳንድ ጎሣ የተወሳሰበ ብርድ ልብስ ሽመና ስለ መሥራታቸው ዕውቅና አላቸው። ሌሎች ጎሣዎች ጌጣጌጥ ከሉልና ከቀይ መንቁራ ወዘተ. ይሠራሉ። ከሁሉ ቀላል ኑሮ በሩቅ ደን ቦታዎች የሚገኙ ጎሣዎች እስካሁን ድረስ በትንፋሽ የሚነፋ ፒፓ (ፍላጻን ለመውረር) ለማደን እንደ መሣርያ ይጠቅማሉ። በፊሊፒንስ ብቻ የሚማሩ የትግል (ቡጢ) ሥነ ሥርዐቶች ለምሳሌ አሚስ እና ኤስክሪማ ይታወቃሉ።

ጨዋታ በፊሊፒንስ በተለይም ቢሊያርድስ (ከረንቦላን የሚመስል)፣ ቦውሊንግሰንጠረዥ (ቼዝ) ይወደዳሉ። እግር ኳስቡቅሻ ደግሞ በጣም ይወደዳሉ።

90 ከመቶ የፊሊፒንስ ኗሪዎች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ናቸው፣ በየከተማውም ስፓኒሾች ከድንጋይ የሠሩ አቡያተ ክርስቲያናት አሁንም አሉ። ሌላ 5 ከመቶ እስላሞች ናቸው፣ የቀሩትም 5 ከመቶ አረመኔ ልማዶች ወይም ሌላ እምነት የሚከተሉ ናቸው።

ብዙ የፊሊፒንስ ኗሪዎች ከቀርከሃ ወይም ዘምባባ እንጨት በተሠራ በቀላል መኖርያ ማደር ይመርጣሉ። ኗሪ ባህሎች ከእስፓንያ፣ ከሜክሲኮ፣ ከፖሊኔዥያ፣ ከአሜሪካ፣ ከቻይና፣ ከሌሎችም እስያዊ አገራት ተጽእኖዎች በመቀላቀሉ፣ እንዲሁም የፊሊፒንስ አበሳሰል ከነዚህ ተጽእኖዎች ሁሉ ይወክላል።