ስሜን ቆጵሮስ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ስሜን ቆጵሮስ - ቀይ

ስሜን ቆጵሮስ (በይፋ፦ «የቱርክ ስሜን ቆጵሮስ ሪፐብሊክ»፤ ቱርክኛ፦ Kuzey Kıbrıs /ኩዘይ ክብርስ/) በቆጵሮስ ደሴት ላይ የምትገኝ አገር ናት።

ቱርክ አገር በስተቀር፣ ከአንዳችም ሌላ አገር ምንም ዲፕሎማቲክ ተቀባይነት የለውም። በተረፈ ሌሎቹ አገራት በይፋ በደቡብ የሚገኘውን የቆጵሮስ ሪፐብሊክን ይግባኝ ይቀበላሉ።

ምጣኔ ሀብቱ በተለይ በቱሪስም ይመሰረታል፤ ቱሪስቶቹ ወይም በአየር ከቱርክ አገር፣ ወይም በመርከብ ይገባሉ። በግል ጀልባ (ያሕት) የሚገቡም አሉ። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ምርቶች የወተት ውጤቶች፣ ሎሚአረቄዶሮድንች ናቸው። ሕዝቡ ቱርክኛ ይናገራልና የእስልምና ተከታዮች ናቸው። ዋንኛው እስፖርት እግር ኳስ ነው። ባሕላቸው በጭፈራና በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በአበሳሰል ወዘተ. እንደ ቱርክ አገር ባሕል ይመስላል።