ክሪሜያ
Appearance
(ከክራይሚያ የተዛወረ)
ክራይሚያ ወይም ክራይሜያ በጥቁር ባሕርና በአዞቭ ባሕር አጠገብ የሆነ ልሳነ ምድር ነው።
ከጥንት ጀምሮ ብዙ ብሔሮች ስለዚሁ ምድር በጦርነት ተዋግተዋል።
ዛሬ ብዙዎቹ ኗሪዎች የሩስኛ ተናጋሪዎች ናቸውና፣ በ2006 ዓም ክፍላገሩ ከዩክሬን ነጻነቱን ካዋጀ በኋላ በቅርቡ ውስጥ ሩስያ ወደ ግዛቷ በሃይል ጨመረችው። ከዚያ ጀምሮ ክፍላገሩ በሩስያ አስተዳደር ስር ቆይቷል። ሆኖም ዩክሬን እስካሁን ይግባኝ ትላለች።
ይህ የሩስያ ድርጊት ከአሥራ አንድ አገራት ብቻ በይፋ ተቀባይነት አገኝቷል፤ እነርሱም አፍጋኒስታን፣ ቦሊቪያ፣ ቤላሩስ፣ ኩባ፣ ኪርጊዝስታን፣ ኒካራጓ፣ ስሜን ኮርያ፣ ሱዳን፣ ሶርያ፣ ቬኔዝዌላ፣ ዚምባብዌ ናቸው። ብዙ አገራት ደግሞ ክፍላገሩ የዩክሬን እንደ ሆነች ብለዋል። በአፍሪካም ብዙዎቹ አገራት እንዲህም እንዲያም ምንም አስተያየት ገና አልሰጡም።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |