መስከረም ፲
Appearance
መስከረም ፲ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፹፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፶፮ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፶፭ቀናት ይቀራሉ።
መስከረም 10፣ *፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የቀድሞዋ ዳሆሚ (አሁን ቤኒን)፤ የቀድሞዋ ኣፐር ቮልታ (አሁን ቡርኪና ፋሶ)፤ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ፤ ቻድ፤ ኮንጎ ሪፐብሊክ፤ አይቮሪ ኮስት፤ ጋቦን፤ ማዳጋስካር፤ ኒጀር፤ ሶማልያ፤ ቶጎ፤ ማሊ፤ ሴኔጋል እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባላት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው ያዘጋጁትን “የታሪክ ማስተወሻ” ላኩ። በመስከረም ወር ፲፱፻፹፮ ዓ/ም በጦብያ መጽሔት ላይ የወጣው ይኼው የትሪክ ማስታወሻ ለሕይወት ታሪካቸው ዋቢ ምንጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረው ኢቲ-ኤጂዩ (ET-AGU) ዲ-ሲ ፫ (Douglas C-47 A -20-DK) አየር ዠበብ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ፣ ከባረንቱ ማረፊያ ሊነሳ ሲያኮበኩብ በአፍንጫው ተደፍቶ ሲከሰከስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም - የቀድሞዋ መካከለኛ አፍሪቃ ንጉዛት መንግሥት (Central African Empire) መሪ ዣን ቢዴል ቦካሳ በፈረንሳይ መንግሥት ዕርዳታ በተደራጀ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወገዱ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት በየዓመቱ በመስከረም ወር በሁለተኛው ሳምንት ዕለተ ሰኞ እንዲከበር በተወሰነው ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ ያለበት ሰንደቅ ዓላማ ቀን።
- ጦቢያ መጽሔት ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፮፤ መስከረም ፲፱፻፹፮ ዓ/ም
- (እንግሊዝኛ) Criminal Acts Against Civil Aviation 1992 / U.S. Department of Tranport, FAA, Office of Civil Aviation Security]]
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/October_20
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |