ክረምት
Appearance
ክረምት'፤ ስርወ ቃሉ ከርም፤ ከረመ ካለው የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ወርኃ ዝናም፣ ወርኃ ነጎድጓድ፣ ዘመነ ባሕር፣ ዘመነ አፍላግ፣ ዘመነ ጠል፣ ዘመነ ደመና፣ ዘመነ መብረቅ ማለት ነው። የክረምት ወቅት ከሰኔ ፳፮ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ነው።
"ደምፀ እገሪሁ ለዝናብ ሶቦ ይዘንብ ዝናብ ይትፌስሑ ነዳያን ደምፀ እገሪሁ ለዝናብ ሶበ ይዘንብ ዝናብ ይፀግቡ ርሁባን" (ሲተረጐም) የዝናብ ኮቴ ተሰማ፤ ዝናብ በዘነበ ጊዜ ነዳያን ይደሰታሉ፤ የተጠሙ የተራቡ ይጠግባሉ፡፡
የወቅት ስም | የመግቢያው ቀን | የማለቂያው ቀን |
---|---|---|
መፀው (አበባ) | መስከረም ፳፮ | ታኅሣሥ ፳፭ |
በጋ | ታኅሣሥ ፳፮ | መጋቢት ፳፭ |
ፀደይ (በልግ) | መጋቢት ፳፮ | ሰኔ ፳፭ |
ክረምት | ሰኔ ፳፮ | መስከረም ፳፭ |
- http://www.eotcmk.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=46&Itemid=1 Archived ኦክቶበር 23, 2010 at the Wayback Machine
- http://www.ethiopianreporter.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2005 at the Wayback Machine