በጋ
Appearance
በጋ ፀሐይ የሚበረታበት፣ ደረቅና ሐሩር የሐጋይ ወራት ተብሎ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ (ቁጥር ያለው ዘመን) መሠረት ከክረምት በኋላ መስከረም ፳፮ ቀን የሚጀምረው የመፀው (አበባ) ወቅት፣ ጊዜውን ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ፈጽሞ ለበጋ ያቀብላል። በጋ የሚያበቃው መጋቢት ፳፭ ቀን ሲሆን ተረካቢው ወቅት ደግሞ ፀደይ (በልግ) ይሆናል።
የወቅት ስም | የመግቢያው ቀን | የማለቂያው ቀን |
---|---|---|
መፀው (አበባ) | መስከረም ፳፮ | ታኅሣሥ ፳፭ |
በጋ | ታኅሣሥ ፳፮ | መጋቢት ፳፭ |
ፀደይ (በልግ) | መጋቢት ፳፮ | ሰኔ ፳፭ |
ክረምት | ሰኔ ፳፮ | መስከረም ፳፭ |