ጥቅምት ፮
Appearance
ጥቅምት ፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፴፮ኛው ዕለት እና የመፀው ፲፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፴ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፳፱ ዕለታት ይቀራሉ።
- በአሜሪካ ይኼ ቀን የዐለቃዎች ቀን (boss’s day) በመባል የተሰየመ ሲሆን፤ ሥራ መያዝንና ሥራ ላይ መሆንን የማክበሪያ ቀን ነው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ የመጀመሪያዋን አቶሚክ ቦንብ አፈነዳች።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በጋማል አብደል ናስር ሞት ምክንያት በግብጽ አንዋር ሳዳት የአገሪቱ ፫ኛ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የዋቢ ሸበሌ ሆቴል ድርጅት በደርግ መንግሥት ተወረሰ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቫቲካን የተሰበሰቡ የዓለም ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳሳት፣ በ ፬፻ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ጣሊያናዊ ያልሆኑትን በ ፖላንድ የክራካው ካርዲናል የነበሩትን ካሮል ዮሴፍ ቮይትዋን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፖፕ) በማድረግ መረጡአቸው። ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በተመረጡ በ ፴፫ ቀናቸው በድንገት በሞት የተለዩትን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስን በመተካት ፪፻፷፬ናው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነዋል።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን የኬፕ ታውን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ደቡብ አፍሪቃዊው ዴዝሞንድ ቱቱ የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀባይነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር የሱዳን ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፰፻፸፱ ዓ/ም - የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት ዴቪድ ግሪን ወይም ዴቪድ ቤንጎርዮን ተወለዱ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ስመ ጥሩው የእስራኤል ጄኔራል፤ እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ሚንስቴርነት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ማዕረግ የበቁት ሞሼ ዳያን በተወለዱ በ፶፮ ዓመታቸው በሞት ተለዩ።
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |