Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

የፈረንሳይ አብዮት

ከውክፔዲያ

የፈረንሳይ አብዮትፈረንሳይ አገር ታሪክ ከ1781 እስከ 1791 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደ ሲሆን በዚህ አብዮት የፈረንሳይ ሕዝብ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረውን የዘውድ አገዛዝ እና ተያያዥ የፊውዳል ሥርዓትን በመገርሰስ፣ አገራቸውን በአዲስ መልክ በሪፐብሊክ ያዋቀሩበት ሂደት ነው።

የአብዮቱ አነሳስ ብዙና በአንድ ጊዜ የተከማቹ ምክንያቶች ነበሩት። አንደኛው ምክንያት የፈረንሳይ ሕዝብ ቁጥር ማደግ ነበር። ከሕዝቡ ቁጥር ጋር አብሮ እየጨመረ የሄደው በትውልድ ሳይሆን በጥረት ባለሃብት የሆነው(ለምሳሌ፣ ነጋዴ፣ አምራች፣ ሐኪም፣ ወዘተ ..) ባጠቃላይ በፈረንሳይኛ ቡርዧ መደብ፣ የፖለቲካ ስልጣን እንደ ባላባቶች ለመያዝ መፈለጉ አንዱ የአብዮቱ መነሻ ነበር። የገበሬው መደብ አባላት በአንጻሩ አብዛኞቹ የራሳቸው መሬት ባለቤት እየሆኑ ስለመጡ፣ በፊውዳል ሥርዓቱ ላይ ከንቀት ጋር የተቀላቀለ ጥላቻ ነበራቸው። ሊያጠፉትም ይፈልጉ ነበር።

በዚህ መሃል፣ የብርሃናት ክፍለ ዘመን የተባለው ከፍተኛ የውይይት፣ ክርክር እና የዕውቀት ስርጭት በፈረንሳይ አገር ይካሄድ ነበር። እነ ባሩክ ስፒኖዛደካርት እና ጆን ሎክ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ያነሷቸው የፍልስፍና ሐሳቦች፣ በዚህ ዘመን ፍሬ ማፍራት ጀመሩ። ቮልቴርሩሶ እና ሞንተስኪ የተባሉ ምሁራን፣ ይህን መነሳሳት በብዙ ጽህፈቶቻቸው በማፋፋም አጠቃላይ ማህበረሳባዊ ለውጥ እንዲነሳ ግድ ሆነ። የብርሃን ክፍለ ዘመን ሃሳቦች በማንበቢያ ቤቶች፣ በገበሬ ማህበራት፣ በክበቦች ይሰራጩ ነበር እና ከፍተኛ መነቃቃት አስነስተው ነበር።

ንጉሱ እና የዘውዱ ስርዓት በበኩላቸው በሚያካሂዱት ብዙ ጦርነት ከፍተኛ የገንዘብ ማባከን ደርሶ ነበርና፣ ይህን ለመሸፈን በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ለመቅረጥ አስበው ነበር። ከዚህ በፊት ቀረጥ የማይከፍለውን የመሳፍንት እና መኳንንት መደብ ሁሉ ቀረጥ ሊያስከፍሉ ሞክረው ከሰፊው ሕዝብ ጋር ብቻ ሳይሆን ደጋፊ ከሆነው መደብ ጋር ሊጣሉ በቁ።

ይህ ሁሉ በሚንተከተክበት በስትወዲያዉ፣ የ1880 ዓ.ም. እርሻ ምርት እጥረት እና ያስከተለው ረሃብ፣ አብዮቱ እንዲፈነዳ አደረገ። ይህ አብዮት በአለም ታሪክ ላይ እስካሁን ድረስ ተጽዕኖ በመፍጠር ይታወቃል።

በአብዮቱ የፈረንሳዩ ንጉስ በአደባባይ በጊዮሎቲን ሲገደል፣ የዘውድ ሥር ዓቱ ተደምስሶ በምትኩ የሪፐብሊክ ሥር ዓት ተቋቁማል። የፊውዳሊዝም ሥር ዓት እንዲሁ በፈረንሳይ በሕግ ታግዷል። አብዮቱ በኋላ ላይ የሽብር መንግስት የተባለውን መንገድ መከተል ሲጀምር ብዙ ደም በማፋሰሱ በተወሰነ ደረጃ ሊጨናገፍ ቢችልም፣ የሕዝብ ሃይል የቱን ያክል የገዘፈ እንደሆነ በማሳየት ዘመናዊ መንግስታትን አወቃቀር እስካሁን ድረስ በተጽዕኖው ስር ያሳድራል።