ነሐሴ ፳፭

ከውክፔዲያ
(ከነሐሴ 25 የተዛወረ)

ነሐሴ ፳፭

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፭ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፲፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፲ ዕለታት ይቀራሉ።

ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፵፱ ዓ/ም የቀድሞዋ ማላያ (የአሁኗ ማሌዢያ) ነጻነቷን ከብሪታንያ ተቀዳጀች።

፲፱፻፶፬ ዓ/ም ትሪንዳድ እና ቶባጎ የሚባሉት የካሪቢያ ባሕር ደሴቶች ነጻነታቸውን ከብሪታንያ ተቀዳጁ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም የኪርጊዝስታን ሪፑብሊክ ከሶቪዬት ሕብረት ሥር ነጻ ወጣች።

፲፱፻፹፬ ዓ/ም በኮንጎ ሪፑብሊክ በተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፓስካል ሊሱባ በፕሬዚዳንትነት ተመረጡ።

፲፱፻፹፱ ዓ/ም የብሪታንያ አልጋ ወራሽልዑል ቻርልስ ባለቤት ዲያናዌልስ ልዕልት በመኪና አደጋ ፓሪስ ከተማ አረፉ።

፳፻ ዓ/ም በመሐንዲስ ኃይሉ ሻውል የሚመራው መስከረም ፲፬ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም የተዋሐደው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ስሙን በመለወጥ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተብሎ ተሰየመ፡፡

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፷፩ ዓ/ም የዓለም የከባድ ሚዛን የቡጢ ውድድር መደብ ቻምፒዮና የነበረው ኢጣልያ አሜሪካዊው ሮኪ ማርሲያኖ አረፈ።

፲፱፻፹፱ ዓ/ም የብሪታንያ አልጋ ወራሽልዑል ቻርልስ ባለቤት ዲያናዌልስ ልዕልት በመኪና አደጋ ፓሪስ ከተማ አረፉ።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]