ሜሪላንድ
| |||||
| [[image:{{{ግዛት_ካርታ}}}]] | |||||
| ዋና ከተማ | [[{{{ግዛት_ዋና_ከተማ}}}]] | ||||
| ትልቋ ከተማ | [[{{{ግዛት_ትልቋ_ከተማ}}}]] | ||||
| አገረ ገዥ | [[{{{ግዛት_አገረ_ገዥ}}}]] | ||||
| የመሬት ስፋት | {{{ግዛት_መሬት_ስፋት}}} ካሬ ኪ.ሜ.(ከአገር {{{ግዛት_መሬት_ስፋት_ከአገር}}}ኛ) | ||||
| የሕዝብ ብዛት | {{{ግዛት_ሕዝብ_ብዛት}}}(ከአገር {{{ግዛት_ሕዝብ_ብዛት_ከአገር}}}ኛ) | ||||
| ወደ የአሜሪካ ሕብረት የገባችበት ቀን |
{{{ግዛት_ሕብረት_ቀን}}} እ.ኤ.ኣ. | ||||
| ላቲቲዩድ (ኬክሮስ) | {{{ግዛት_ላቲቲዩድ}}} | ||||
| ሎንግቲዩድ (ኬንትሮስ) | {{{ግዛት_ሎንግቲዩድ}}} | ||||
| ከፍተኛው ነጥብ | {{{ግዛት_ከፍተኛ_ነጥብ}}}ሜ. | ||||
| ዝቅተኛው ነጥብ | {{{ግዛት_ዝቅተኛ_ነጥብ}}}ሜ. | ||||
| አማካኝ የመሬት ከፍታ | {{{ግዛት_አማካኝ_ከፍታ}}}ሜ. | ||||
| ምዕጻረ ቃል | {{{ግዛት_ምዕጻረ_ቃል}}} | ||||
| ድረ ገጽ | [{{{ግዛት_ድረ_ገጽ}}}] | ||||
ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።
የህዝቡ የዘር ክፍልፋይ
- 62.1%-ነጭ
- 27.9%-ጥቁር
- 4.3%-ላቲን
- 4.0%-ኤሲያን
- 0.3%-ቀይ ህንድ
- 2.0%-ክልስ
የሐይማኖት ክፍልይ
- ክርስቲያን-82%
- ፕሮቴስታንት-56%
- ባፕቲስት-18%
- ሜቶዲስት-11%
- ሌላ ፕሮቴስታንት-27%
- ሮማን ካቶሊክ-23%
- ሌላ ክሪስቲያን-3%
- ፕሮቴስታንት-56%
- ይሁዳ-3%
- ሌላ ሐይማኖት-15%
- አናፖሊስ - የስቴቱ ዋና ከተማ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል ማሰልጠኛ የሚገኝበት ቦታ
- ባልቲሞር - በሕዝብ ብዛት ከስቴቱ አንደኛ
- ኮሌጅ ፓርክ - ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ የሚገኝበት ቦታ
- ኮለምቢያ - ከስቴት 2ኛ ትልቅ ከተማ
- ኦሽን ሲቲ - ታዋቂ የባሕር ዳር መዝናኛ (ቢች) ያለበት ሥፍራ
- ሮክቪል - የሞንትጎምሪ ክልል (ካውንቲ) የንግድ ማዕከል
- ሳሊስበሪ - የዴልማርቫ ልሳነ ምድር (ፔኒንሱላ) ትልቁ ከተማ እና የንግድ ማዕከል
- ታውሰን - የባልቲሞር ክልል (ካውንቲ) መንግስት መቀመጫ
| ካውንቲ | የተመሠረተበት ዓ.ም.(እ.ኤ.ኣ.) | የመንግስት መቀመጫ |
| አለገኒ ካውንቲ | 1789 | ከምበርላንድ |
| አን አረንዴል ካውንቲ | 1650 | አናፖሊስ |
| ባልቲሞር ካውንቲ | 1659 | ታውሰን |
| ካልቨርት ካውንቲ | 1654 | ፕሪንስ ፍሬድሪክ |
| ካሮላይን ካውንቲ | 1773 | ዴንተን |
| ካሮል ካውንቲ | 1837 | ዌስትሚንስትር |
| ሲሲል ካውንቲ | 1672 | ኤልክተን |
| ቻርልስ ካውንቲ | 1658 | ላ ፕላታ |
| ዶርቸስተር ካውንቲ | 1668 | ኬምበሪጅ |
| ፍሬደሪክ ካውንቲ | 1748 | ፍሬደሪክ |
| ጋሬት ካውንቲ | 1872 | ኦክላንድ |
| ሀርፎርድ ካውንቲ | 1773 | ቤል ኤር |
| ሀዋርድ ካውንቲ | 1851 | ኤሊኮት ሲቲ |
| ኬንት ካውንቲ | 1642 | ቼስተር ታውን |
| ሞንትጎመሪ ካውንቲ | 1776 | ሮክቪል |
| ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ | 1695 | አፐር ማርልቦሮ |
| ክዊን አን ካውንቲ | 1706 | ሴንተርቪል |
| ሴንት ሜሪ ካውንቲ | 1637 | ለናርድታውን |
| ሶመርሰት ካውንቲ | 1666 | ፕሪንስስ አን |
| ታልቦት ካውንቲ | 1662 | ኢስተን |
| ዋሽንግተን ካውንቲ | 1776 | ሄገርስታውን |
| ዊኮሚኮ ካውንቲ | 1867 | ሳሊስበሪ |
| ዎርስተር ካውንቲ | 1742 | ስኖው ሂል |
|
|