Jump to content

ሊያ ከበደ

ከውክፔዲያ
ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደ በእ.አ.አ. 2008 የትራይቤካ የፊልም ፌስቲቫል ላይ

ሊያ ከበደ (እንግሊዝኛ: Liya Kebede) የተወለደችው በእ.አ.አ. ጃንዌሪ 3፣ 1998ሲሆን ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ሡፐር ሞዴል፣ ተዋናይት፣ የልብስ ዲዛይነር እንዲሁም የአለም የጤና ድርጅት በእናቶች፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናት እና የሕፃናት ጤና ጥበቃ አምባሳደር ናት፡፡ ሊያ "ቮግ" በተባለ የአሜሪካ የፋሽን መፅሔት ላይ ሁለት ጊዜ የውጭ ሽፋን ላይ በዋናነት በመውጣት ትታወቃለች። እንደ ፎርብስ መረጃ መሠረት በእ.አ.አ. 2007 አመት ከዓለማችን 11ኛ ከፍተኛ ተከፋይ ሡፐር ሞዴልነት ደረጃን አግኝታለች።

የህይወት ታሪክ [ከጃንዌሪ 3 1978 እስከ አሁኑ ጊዜ][ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሊያ ከበደ የተወለደችው በኢትዮጵያ ውስጥ በዋና ከተማአዲስ አበባ እ.አ.አ. ጃንዌሪ 3፣ 1978 ነው። አንድ የፊልም ዳይሬክተር ነበር Lycee Guebre Mariamን በመታደም ላይ ሳለች ያያት እናም ከፈረንሣይ የሞዴል ባለሙያ ጋር ያስተዋወቃት። ጥናቷን ካጠናቀቀች በኋላ ነበር ከፐርሺያ ኤጀንሲ ጋር ለመስራት ወደ ፈረንሣይ ያቀናችው። በኋላም ወደ ኒው ዮርክ ከተማ ተዛወረች። እናም የውጭው አለም የፋሽን መድረክ ከሀገርኛው ጋር ፍፁም የተለያየ መሆኑን ተገነዘበች።

የሞዴልነት ሥራ [ከ1978 እ.አ.አ. ጀምሮ][ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሊያ ትልቁ ወደሆነው የህይወቷ ምዕራፍ የተሸጋገረችው ቶም ፎርድ የተባለ ግለሠብ Gucci ለተባለ የክረምት ፋሽን ትርኢት እ.አ.አ. 2000 ላይ እንድትካፈል ከጠየቃት በኋላ ነበር። የሊያ እውቅና እጅጉን የጨመረው በእ.አ.አ. 2002 Paris Vogue መፅሔት እትም ላይ የውጭ ሽፋን ከሠጣት እና ሙሉ ይዘቱን ማለት ይቻላል ስለ እርስዋ ካደረገ በኋላ ነበር።

ሊያ በተመሳሳይ በጣልያንጃፓንአሜሪካስፔንፈረንሣይ Vogue መፅሔት እትሞች ላይ እና በTime's Style & Design ላይ የሽፋን ቦታን በተለያዩ ጊዜያት አግኝታለች። እ.አ.አ. በ2003 ለEstée Lauder ኮስሞቲክስ በ57 አመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ተወካይ በመሆን የ3 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈርማለች።

በፎቶ ትዕይንቶች ላይ ጎልተው ከሚታዩ ጥቂት የአፍሪካ ሞዴሎች አንዷም ናት። በነዚህም ታዋቂነቶቿ እና በመልካም ተግባሯ እ.አ.አ. በ2005 የአለም የጤና ድርጅት በእናቶች፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናት እና የሕፃናት ጤና ጥበቃ አምባሳደር ሆናለች። እ.አ.አ. በ2005 American Vogue መፅሔት ይህንኑ ሠብዓዊ ተግባሯን በመጥቀስ እና የፊት ገፅ ላይ ምስሏን በማውጣት ከጥቂት ጥቁር ሞዴሎች ተርታ እንድትሰለፍ አስችሏታል። በአንድ ወቅት ሊያ ስለአፍሪካ ስትናገር "ይህንን ስሜት የፈጠረብኝ አፍሪካ ውስጥ ተወልጄ ማደጌ ነው። በድኅነት ተከቦ እየኖሩ ስለድኅነት አለማሰብ ፈፅሞ የማይቻል ነገር ነው። ልጅህን በምትወልድበት በዚያችው ደቂቃ ነው ለልጅህ የተሻለች ዓለም ትተህ ማለፍ እንዳለብህ ማሰብ የምትጀምረው" ብላ ነበር።

ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደ በእ.አ.አ. 2008 የCarolina Herrera የፋሽን ቴይንት ላይ

በጁሌይ 2007 እ.አ.አ. ላይ ፎርብስ በግንቦት 10 ቀን 2010 የታይም መፅሔት እትም ላይ "ተፅዕኖ ማሣደር ከሚችሉ 100 የአለማችን ምርጥ ሠዎች (The 100 most INFLUENTIAL PEOPLE IN THE WORLD) ብሎ ካወጣቸው ታዋቂ ሠዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ሊያ ከበደ አንዷ ነበረች። መፅሔቱ Leaders, Artists, Thinkers እና Heroes በሚሉ ታላላቅ ዘርፎቹ ስር ነው የሠዎቹን ስም ዝርዝር ያሠፈረው። ከሊያ ከበደ ጋር ከተጠቀሡት ታላላቅ ሠዎች መካከል ዲዲዮር ድሮግባስኮት ብራውንጀምስ ካሜሮንዛሃ ሀዳድቤንስቴለርአሽተን ኩቸርሣራ ፖሊንቢል ክሊንተንካትሪን ቢግሎውሳንድራ ቡሎክሳይመን ኮዌልሀን ሀንኦፕራ ዌንፍሬይባራክ ኦባማ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

2.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ከዓለማችን 15 ከፍተኛ ተከፋይ ሡፐር ሞዴሎች 12ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

የፊልም ትወና በታላቁ የሆሊውድ መድረክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሊያ በተለያዩ እንደ The Good Shepherd እና Lord of War የተባሉ የሆሊውድ ታላላቅ ፊልሞች ላይ እንደ አነስተኛ ተዋናይትነት ተሳትፋለች። ነገር ግን በ2009 እ.አ.አ. የትለቀቀው Desert Flower የተሠኘው በመሪ ተዋናይትነት የቀድሞዋን ሡፐር ሞዴል Waris Dirieን በመሆን የተሳተፈችበት ፊልም ከፍተኛ ዕውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።

ለምለም ባህላዊ የህፃናትና ሴቶች ልብስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የለምለም ሎጎ

በጁላይ 2007 እ.አ.አ. ላይ ፎርብስ ለምለም እ.አ.አ. በ2008 የተከፈተ የሊያ ከበደ የልብስ አምራች ድርጅት ነው። ድረ-ገፁ http://www.lemlem.com/ ሲሆን የሀበሻ እጅ ጥበብ ያረፈባቸውን የህፃናትና የሴቶችን ልብሶች ያመርታል። ሊያ ይህን የጀመረችው የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ እና የሀገሯን ኢኮኖሚ ለማገዝ ብላ መሆኑ ታውቋል። ምርቶቹ በBarney’sJ.CrewNet-a-Porter.com እና በሌሎች ቡቲኮች ይሸጣሉ። ሠዎችን እንደመርዳት የሚያስደስት ነገር የለም የምትለው ሊያ ይህ ጅምር ለሀገሯ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ታምናለች።

የግል ህይወት [ቤተሠባዊ ህይወት][ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሊያ ከበደ የhedge fund ማናጀር ከሆነው ባለቤቷ ኬሲ ከበደ ጋር በትዳር የተሳሰሩት እ.አ.አ. በ2000 ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ናት። ስሁል የሚባለው ልጇ በእ.አ.አ. በ2001 የተወለደ ሲሆን ሬይ የተባለችው ልጇ ደግሞ እ.አ.አ. በ2005 ነው የተወለደችው። እ.አ.አ. በ2007 ቤተሠባቸው በኒው ዮርክ ከተማ መኖር ጀመረ። ሊያ ከበደ በግሏ የምታስተዳድረው ሳይት ያላት ሲሆን አድራሻውም http://liyakebede.com/ ነው። በዚህም ድረ-ገፅ የራሷን ማስታወቂያ እና የዕርዳታ ጥሪዎቿን ለማስተላለፊያነት ትጠቀምበታለች።