ታኅሣሥ ፲፪
Appearance
ታኅሣሥ ፲፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፩ኛ ቀን ሲሆን፤ ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፷፬ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማርቆስ እና ዘመነ ማቴዎስ ደግሞ ፪፻፷፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፲ ዓ/ም - በዘመነ መሳፍንት ፮ ጊዜ ከንጉሥነት ሥልጣናቸው የተሻሩት እና የነገሡት ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ በዚህ ዕለት በትግሬው መሥፍን በራስ ወልደ ሥላሴ ዘመን አርፈው፣ አክሱም ጨለቆት ሥላሴ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የጎጃሙ ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት አማቻቸው የነበሩትን ደጃዝማች አበራ ካሣን እና ወንድማቸውን ደጃዝማች አስፋ ወሰን ካሣን ‘አይዟችሁ አትነኩም’ ብለው አታለው ካስገቡ በኋላ አሳልፈው ለፋሺስት ኢጣልያ ኃይሎች አስረከቧቸው። የጣልያኖቹም ጄኔራል ትራኪያ ወንድማማቾቹን ፍቼ ላይ በዚህ ዕለት አስረሽኖ አንገታቸውን አስቆርጦ ገደላቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ የሱዳን ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት፤ የላይቤሪያ ምክትል ፕሬዚደንት እና የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ስለኢየሩሳሌም ከሮማው ጳጳስ እና ከኢጣልያ ፕሬዚደንት ሊዮኔ ጋር የሦስት ቀን ውይይት ለማካሄድ ሮማ ገቡ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት "የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብአዊነት"ን (የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም) በይፋ ካወጀ በኋላ፣ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው "ብሔራዊ የዕድገት በኅብረት የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ" የተሰኘ ፷ ሺ የሁለተኛ ደረጃ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን በመላ አገሪቱ አሰማራ። የጊዘውም መፈክር ፣"በዕድገት በኅብረት - እንዝመት፣ ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት" የሚል ነበር[1]
- ፲፰፻፲ ዓ/ም - ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ አርፈው አክሱምጨለቆት ሥላሴ ተቀበሩ። በወቅቱ እዚያው ይኖር የነበረው እንግሊዛዊው ናትናኤል ፒርስ ዓፄው ሲሞቱ እድሜያቸው ፷፮ ዓመት እንደነበረና ዕለቱ የቅዱስ ሚካኤል እና የቅዱስ ፋሲለደስ ክብረ በዓል ስለነበር የሬሳ ሳጥን መሥሪያ እንጨት መቁረጥ ባለመቻሉ ያለ ሬሳ ሳጥን ተቀበሩ ይላል። [2]
- ^ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ትግላችን ፦የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ [ቅፅ ፩]፤ ታኅሣሥ ወር ፳፻፬ ዓ.ም.
- ^ Peare, Nathaniel; "The Life and Adventures of Nathaniel Pearce", Vol II ; London (1831); page 168
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- ሪፖርተር
- (እንግሊዝኛ) Mockler, Anthony; Haile Selassie’s War (2003)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |