መንግስቱ ኃይለ ማርያም

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

መንግስቱ ኃይለማሪያምግንቦት 271941 እ.ኤ.አ.አዲስ አበባ ተወለዱ። አባታቸው ሃምሳዓለቃ ሃይለማሪአም ወልዴ፣ እናታቸው ብዙነሽ ተሰማ ነበሩ

መንግስቱ ኃይለ ማርያም 1986

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም' ከ1966 እስከ 1983 ዓ.ም. (1974 እስከ 1991 እ.ኤ.አ.) ለ17 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ ነበሩ። ወደ ስልጣን የወጡት በደርግ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በመገልበጥ ሲሆን ተቃናቃኝቻቸው የነበሩትን የቅርብ ጓደኞቻቸውንና የደርጉን መሥራቾች ባማስወገድ ብቸኛ የአብዮቱ መሪ ሆነው ከቆዩ በኋላ በመለስ ዜናዊ በሚመራው መራሹ የኢሓዴግ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን በ1983ዓ.ም ከስልጣን ተወገዱ። በአሜሪካ ሲ አይ ኤ እርዳታ አገር ጥለው በመኮብለል ዚምባብዌ ሀራሬ ተሸሽገው ይኖራሉ።

መንግሥቱ ኃይለማሪያም ወደ ርዕሰ ብሄርነት ሥልጣን ብቅ ሲሉ ገና የ፫፯ ዓመት ወጣት የነበሩ ሲሆኑ በዘመቻ ቀይ ሽብር የብዙ ሺህ ወጣቶችን መጨፍጭፍ ከመጀመራቸው በፊት በሀረር የ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር። በወቅቱ በክፍለ ጦሩ አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሓይሌ ባይከዳኝ የሚባሉ ኮ/ መንግስቱን በባህሪያቸው በመጠርጠራቸው ከአጠገባቸው ዞር ለማድረግ ወደ ኦጋዲን አዛውረዋቸው እንደ ነበር ይነገራል። በእዚያም ጥቂት ጊዜ በኋላ ለትምህርት ወደ አሚሪካ ሜሪላንድ ለወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት ተላኩ። ከትምህርት ሲመለሱም በ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።

ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ሶማሊያ በሶቭየቶች ተደግፋ ሀገራችንን ድንገት ወረረች። በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩትን ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተርን ፈጣን ወታደራዊ እርዳታ ጠይቀው እሳቸውም ደርግ ከራሺያ ጋር በጀመረው ወዳጅነት በመጠራጠራቸው የመግሥቱን ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀሩ። በእዚህም ምክንያት አማራጭ ያጣው ደርግና መንግሥቱ ሀገሪቱ በከፍተኛ ስጋት ላይ በመውደቋ የግድ ወደ ሞስኮ መሳሪያ ልመና ልኡካን ላኩ። በሌላ በኩል ሞስኮ ከሶማሊያ ጋር ጥቅምዋን በማወዳደር ለመንግስቱ መሳሪያ መስጠት ካስፈለገ በፊርማ ሶሻሊስት ካምፐ መግባቱን እንዲያረጋግጡ ስለ ጠየቀች ኮ/መንግሥቱ ይህን በማድረጋቸው በይፋ የሚመሩት አብዩት የሌኒኒስት ማርክሲስት መሆኑን በአዋጅ አሳወቁ። ኮ/መንግሥቱ የቼ ጉቬራና የማኦ ሴቱንግ ሕይወት ታሪክ መጻህፍቶች ከማንበብ በስተቀር ስለ ሶሻሊዝም ከወሬ ባለፈ የሚያውቁት ጥልቅ እውቀት አልነበረም። ከስምምነቱም በሁዋላ በ፪ ወር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሚሊዮን ዶላር ታንክና የጦር መሣሪያ እርዳታ ማግኘት ብቻ ሳይሆን በሞስኮ በኩል የኩባን የጦር አማካሪዎች በማግኘታቸው የወራሪውን የሶማሊያን ኃይል መመከት ችለዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ የጭንቅ ጊዜ ጥያቄ መላሽ ሆና ባለመገኘትዋ መንግስቱ በስልጣን አስከቆዩበት ዘመን ሁሉ በዋና ጠላትነት ፈረጁ። አንዳንድ ሚሲዮናዊያንንም ከአገር አባረሩ።

በወቅቱ በአገር ውስጥ ግንባር ቀደም ተቃናቃኝና ተቃዋሚ ከነበረው ከኢህአፓ ጋር የከተማ ለከተማ ውጊያና መገዳደል ተጀመረ። ሁለቱም ወገኖች ቀን በቀን ግድያም ለብዙ ወጣትና አዋቂ እልቂት ምክንያት ሆኑ። መንግሥቱ ኃ/ማሪያም በወታደራዊ አመራር ውስጥ የተከስተው የስልጣን ዝቀትና ምግባረ ብልሹነት፤ የደህንነቱ ክፍል በሁለት ቢላዋ መብላት ተደማምሮ ውድቀታቸውን እንዳፋጠነው የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራል። በስተመጨረሻ አከባቢ እርሳቸውን የተቃወመውን ሁሉ በረጋ መንፈስ ልዩነቶቹን በመወያየት እንደመፍታትና ምህረት ማድረግ ሲገባቸው የሕዝቡንና የወታደሩን የልብ ትርታ መስማት ስለተሳናቸው ውድቀታቸውን እንዳፋጠነው ታዛቢዎች ይናገራሉ። በኮ/ መንግሥቱ ወታደራዊ አስተዳደር ዘመን ብዙ የተማሩና ተተኪ እማይገኝላቸው ምሁራንን ኢትዮጵያ አጥታለች። እርሳቸውም ከህሊናቸው ፍርድ ሳይተርፉ በቁም እስር ዚምባብዌ በአጥር ተከልለው እድሜያቸውን እየገፉ ነው።

እ.ኤ.አ. በ 1995 መንግስቱ በኤርትራዊ ዜጋ በቤቱ አቅራቢያ የግድያ ሙከራ ደርሶበታል፡፡[1] መንግሥቱ (የቀድሞው) ርዕሰ ብሔር ማንኛውም መሪ ላይ ሊከሰት የሚችል ሕፀፅ ነው ያለባቸው...ስለ ሐገር ስለ ብሔራዊ ክብር እና ኩራት ግን እርሳቸው !ብልሃት ከማነሱ የተነሳ በቀር ከፊት ቢሠለፉ የሚያምርባቸው ናቸው...ይኸውና ያነን ገፅታ ላለመድገም የሚታገለው ዐብይስ እየተተቸ አይደለም ያለው?ሐገርን መምራት ከባድ!!!! ነው ካልሰራ ሊተች ይገበዋል እሱ ከማ በልጦ ነው ሲቀጥል ደሞ በጥላቻ ስሜት አንፍሰስ ሰራና አልሰራም እያልን እንገምግም ደሞ መንግስቱን ጭራቅ አስመስሎ ማቅረብ ደስ አይልም እንኩዋን መንግስቱ ሂትለርም የሰራቸው ጥሩ ስራ አሉት ስንፅፍና ስናወራ በማነፃፀር ይሁን ባይ ነኝ ሲጀመር እናንተ ይሄንን ለመፃፍ ብቁ አደላችሁም ዝም ብለው ከሚፈነጩት ውስጥ ናችሁ አንብቡ በደንብ ከዛ ትፅፋላችሁ ሳያነቡና ታሪክን ሳያገላብጡ ወተት እንደጠገበች ጥጃ መፈንጨት መጨረሻው ገደል ነው!

የሥራ ባልደረባውን ከግዳጅ መልቀቅ በኋላ ሮበርት ሙጋቤ በ 2017ምንም እንኳን ውሳኔው ቢረሳም ኢትዮጵያ ለእሱ የበለጠ መስጠትን አስብ ነበር ፡፡

ጠ / ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በከፍተኛ ትችት የተነሳውን ፎቶግራፍ ከወሰዱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በማኅበራዊ ሚዲያ ፎቶግራፍ ላይ ፎቶግራፍ በመለጠፍ ተተች ፡፡[2][3]

  1. ^ https://apnews.com/6970c33beaea93cefcb9e1355328f5a8
  2. ^ http://www.madote.com/2018/08/why-photo-of-mengistu-haile-mariam-has.html
  3. ^ https://borkena.com/2018/08/01/hailemariam-desalenge-met-colonel-mengistu-hailemariam-in-zimbabwe/