Jump to content

ታምራት ላይኔ

ከውክፔዲያ

ታምራት ላይኔኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰው ነበሩ። ደርግን ለማስወገድ በተደረገው የትጥቅ ትግል፣ መጀመርያ የኢህአፓ ታጋይ፤ ከዛም ኢህአፓ ሲዳከም፤ ኢህድን (የኢትዮጵያ ህዝቦች  ዲሞክራቲክ ንቅናቄ) መስራችና አመራር ነበሩ። ቆራጥ የወታደራዊ አመራርና ጎበዝ ገጣሚ እንደነበሩ የትግል አጋሮቻቸው ይመሰክራሉ። የኢሕአዴግ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ በሙስና ተከስሰው የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው። ከ18ቱ ዓመት 12ቱን ከጨረሱ በኋላ በታኅሣስ ወር አጋማሽ 2001 ዓመተ ምሕረት በአመክሮ ተፈቱ። በእስር ቤት በቆዩበት ጊዜ ከከሃዲነት ወይም አምላክ የለሽነት ወደ አማኝነት የተለወጡ ሲሆን ሲፈቱ የመሰከሩትም ይህንኑ ነበር። አንዳንድ ወሬዎች እንደሚናፈሱት ሆነ ግን 12 ጻመት ወሀኒ ያወረዳቸው ሙሰና ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ሽኩቻም ነው ይባላል።

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]