1929
Appearance
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1890ዎቹ 1900ዎቹ 1910ሮቹ - 1920ዎቹ - 1930ዎቹ 1940ዎቹ 1950ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1926 1927 1928 - 1929 - 1930 1931 1932 |
1929 ዓመተ ምኅረት
- ኅዳር ፳፩ - ክቡር ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ በአሌልቱ ሜዳ ላይ ሦስት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፣ ከጠላት በኩል የኢጣሊያ ፋሽስቶች ፺፮ መኮንኖችና ወታደሮች ተግድለዋል።
- ታኅሣሥ ፩ - በብሪታንያ በንጉሡ የፍቅረኛቸውን ምርጫ ምክንያት በተከሰተው ቀውስ፥ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ሥልጣናቸውንና ዘውዳቸውን መልቀቅ የሚያስችላቸውን ህግና ስምምነት ፈረሙ።
- ታኅሣሥ ፲፱ - በባሌ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ቡላንቾ (አርበጎና) የሚባል ሥፍራ ላይ ሙሴ ቀስተኛና ራስ ደስታ ዳምጠው ተገናኝተው ለሁለት ሰዓት ያህል ተወያዩ።
- ጥር ፲፪ - የፋሺስት ኢጣልያ የጦር ዓለቃ ማርሻል ግራትዚያኒ በራሡ መሪነት የራስ ደስታ ዳምጠውን ሠራዊት በሲዳሞ እና የደጃዝማች ገብረ ማርያምን ሠራዊት በባሌ ለመውጋት ዘመተ።
- ጥር ፲፫ - ጃንሆይ በእንግሊዝ በስደት ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ (በኋላ አቡነ ባስልዮስ) ጽላቱ ለምስካዬ ኅዙናን መድኅኔ ዓለም ቤተክርስቲያን እንዲልኩላቸው ደብዳቤ ላኩ።
- ጥር ፳፯ - የኢትዮጵያ መላክተኛ በብሪታኒያ አዛዥ ወርቅነህ የሹመት ማስረጃቸውን ለንጉሡ ኤድዋርድ 8ኛ አቅርበዋል።
- የካቲት ፲፪ - ግራዚያኒን ለመግደል በተደረገው ሙከራ የስንዱ ገብሩ ወንድም መሸሻ ገብሩ አሉበት በመባል ይታሰሱ ስለነበር ሰንዱ ወንድማቸውን ከአደጋ ለማዳን ሲሞክሩ በድጋሚ በፋሺስቶች እጅ ወደቁ። ጸሐፊው ተክለጻድቅ መኩርያ ደግሞ በዚህ ቀን ተማረኩ።
- የካቲት ፲፭ - ራስ ደስታ ቡታጅራ አካባቢ ላይ በትግራይ ተውላጅ ደጃዝማች ተክሉ መሸሻ ተያዙ።
- የካቲት ፲፮ - በግራትዚያኒ የሚመራ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በዝዋይ አካባቢ የጦር አዝማቾቹን የራስ ደስታ ዳምጠውን እና የደጃዝማች በየነ መርዕድን አርበኞች ድል አደረጉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች ሕይወታቸውን በዚህ ዕለት ሰዉ። ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ በጥይት ደበደቧቸው።
- መጋቢት ፪ - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ
- ሚያዝያ ፳፫ - አርበኛው ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን ተማም ከሚባለው ሥፍራ ላይ በጠላት እጅ ተማረኩ።
- ሰኔ ፲ - አርበኛው በላይ ዘለቀ በዋሻ ተከበበ።
ገና ያልተወሰነ ቀን፦
- የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሮዘቨልት በምርጫ ለሁለተኛ የ4 አመት ዘመን ተመለሱ።
- ኢንተርሊንጉዋ ሰው ሰራሽ ቋንቋ መጀመርያ ተፈጠረ።
- መስከረም ፲፮ - የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት የኔልሰን ማንዴላ የመጀመሪያ ሚስት የነበሩት ዊኒ ማንዴላ ተወለዱ።
- ጥቅምት ፳፩ - ቦናንዛ በሚባለው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ትርዒት ላይ ሊትል ጆን ካርትራይትን ሆኖ በመጫወት በዓለም ስመጥሩነትን ያተረፈው ተዋናይ ማይክል ላንደን
- ሚያዝያ ፲፬ - አሜሪካዊው ተዋናይ ጃክ ኒከልሰን በኒው ዮርክ ከተማ ተወለደ።
- ሚያዝያ ፳ - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን አብደል ማጂድ አል ቲክሪቲ በዚህ ዕለት አል አውጃ በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።