Jump to content

ኢንተርሊንጉዋ

ከውክፔዲያ

ኢንተርሊንጉዋ1929 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈጠረ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ከኤስፔራንቶና ከኢዶ በኋላ በተናጋሪዎች ስፋት ሦስተኛው ሠው ሠራሽ ቋንቋ ነው። የተለቀመው በተለይ ከእንግሊዝኛ፣ ከፈረንሳይኛ፣ ከጣልኛ፣ ከእስፓንኛና ከፖርቱጊዝኛ ስለ ሆነ ቋንቋው ከሁሉ እንደ ሮማይስጥ ይመስላል። ከነዚህ 5 ልሳናት ቀጥለው ጀርመንኛመስኮብኛ በ2ኛ ደረጃ የኢንተርሊንጉዋ ምንጮች ናቸው። የቋንቋው ስም ከሮማይስጥ ቃላት inter (መካከል) እና lingua (ልሳን) ደርሷል። በየአሕጉሩ ጥቂት ሰዎች ያውቁታል።