1944
Appearance
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1910ሮቹ 1920ዎቹ 1930ዎቹ - 1940ዎቹ - 1950ዎቹ 1960ዎቹ 1970ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1941 1942 1943 - 1944 - 1945 1946 1947 |
1944 አመተ ምኅረት
- ጥቅምት ፲፮ ቀን - በብሪታንያ ብሔራዊ ምርጫ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበሩት በዊንስተን ቸርቺል የሚመራው የኮንሰርቫቲቨ ፖለቲካ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቸርቺልም ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ።
- ታኅሣሥ ፪ ቀን - የአንበሳ አውቶቡስ ህጋዊ ሰውነት በማግኘት በአክሲዮን ከተቋቋመ በኋላ አረንጓዴና ቢጫ የተቀቡ ፲ አውቶቡሶችን ይዞ ሥራ ጀመረ፤ እነዚህም አውቶቡሶች በከተማዋ አራት መስመሮች ላይ ብቻ የተሰማሩ ነበሩ።
- ታኅሣሥ ፲፬ ቀን - እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኢጣልያ ቅኝ ግዛትነት፡ እስከነጻነት ደግሞ በብሪታንያ እና ፈረንሳይ ሥር የነበረችው ሊቢያ ነጻ ሆነች። 1 ኢድሪስ የሊብያ ንጉሥ ሆኑ።
- ጥር ፲፫ ቀን - ለአዲስ አበባ ሕዝብ የውሃ አገልግሎት የሚሰጠው የገፈርሳ ግድብ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመረቀ።
- የካቲት ፩ ቀን - በታላቋ ብሪታኒያ እና ሰሜን አየርላንድ ንጉዛት ልዕልት ኤልሳቤጥ አባታቸው ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ ሲያርፉ ዙፋኑን ተቀብለው ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ሆኑ።
- የካቲት ፰ ቀን - የብሪታንያ ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ በዊንድሶር ግምብ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ውስጥ ተቀበሩ።
- ሚያዝያ ፫ ቀን - የአዲስ አበባው ሊሴ ገብረ ማርያም ትምሕርት ቤት ተመረቀ።
- ሚያዝያ ፳፬ ቀን - ‘ደ ሀቪላንድ-ኮሜት’ የተባለው የዓለም የመጀመሪያው የተሳፋሪ ጄት አየር-ዠበብ የመጀመሪያ በረራውን ከሎንዶን እስከ ጆሃንስበርግ ድረስ አከናወነ።
- ሐምሌ ፲፮ ቀን - በጋማል አብደል ናስር የተመሠረተው የግብጽ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በጄነራል ሙሐመድ ናጊብ መሪነት ንጉሥ ፋሩቅን ገለበጠ።
- ሐምሌ ፲፱ ቀን - የግብጽ ንጉሥ ፋሩቅ ዙፋናቸውን ለልጃቸው ንጉሥ ፉዋድ ለቀቁ።
- ነሐሴ ፭ ቀን - በዮርዳኖስ ሐሺሚ ንጉዛት ንጉሡ ታላል በአዕምሮ ሕመምተኛነት ምክንያት በአገሪቱ ምክር ቤት ሸንጎ «ለሥልጣን ብቃት የላቸውም» ተብለው ሲሻሩ ገና አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጃቸው አልጋወራሹ በንጉሥነት እንደተኳቸው ይፋ ተደረገ። ንጉሥ ሁሴን የልደታቸው ዕለት ኅዳር ፯ ቀን ፲፱፻፵፮ ዓ/ም የንግሥ ስርዓታቸው ተከናወነ።
- የሰሎሞን ደሴቶች ዋና ከተማ በኦፊሴል ከቱላጊ ወደ ሆኒያራ ተዛወረ።
- መስከረም ፳፭ ቀን - ቦብ ጌልዶፍ (ሮበርት ፍረደሪክ ዜኖን ጌልዶፍ Robert Frederick Zenon Geldof) የተባለው የአየርላንድ ዜጋ ተወለደ።
- ኅዳር ፲፮ ቀን - ደራሲው አጥናፍሰገድ ኪዳኔ አዲስ አበባ ተወለደ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |