ኅዳር ፯
Appearance
ኅዳር ፯ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፯ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፱ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፰ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፫፻፸፯ ዓ/ም - ንግሥት ጃድዊጋ በፖሎኝ ንጉሥ ተብላ በወንድ ስም ዘውድ ጫነች። ከሞተችም በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ሄድዊግ ብሏታል።
- ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - ከግብጽ ሠራዊቶች ጋር ጉንደት በተባለ ሥፍራ ላይ የዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው ወገኖቻችን በግብጾች ላይ ድል ተቀዳጁ።
- ፲፱፻፴፰ዓ/ም - በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምሕርት፤ ሰገላዊ እና ባህላዊ ድርጅት (UNESCO) ተመሠረተ። የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ፓሪስ ከተማ ላይ ነው።
- ፲፱፻፷፪ዓ/ም - በደጃዝማች ታከለ ወልደ ኃዋርያት መሪነት የተደራጀ የመኮንኖች ቡድን ንጉሠ ነገሥቱን ለመግደል ያደረገው ሙከራ በደኅንነትና ጸጥታ አባላት ተደርሶበት ከሸፈ። ደጃዝማች ታከለም እጃቸውን ላለመስጠት ቆርጠው እራሳቸውን ገደሉ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቃሊቲ የምግብ ማሸጊያ ፋብሪካ በቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ሕገ ወጥ በሆነ የተያዘ ነው በሚል የኢትዮጵያ ግዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) በመንግሥት ስም ወረሰው።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - ደጃዝማች ታከለ ወልደ ኃዋርያት
- {{en]] P.R.O.,FCO 371/536 Annual Review of 1969
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |