Jump to content

ኅዳር ፲፮

ከውክፔዲያ

ኅዳር ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፮ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፱ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዚህ ዕለት በዓለም ዙሪያ ብዙ ተፈጥሮአዊ ሁከቶች የብዙ ሕዝቦችን ሕይወት ማጥፋታቸው በታሪክ ተመዝግቧል። ለምሣሌ፦

  • ፲፫፻፴፮ ዓ.ም. በሰሜናዊ የሜዲተራንያን ባሕር በተለይም ከኢጣልያ በስተምዕራብ በሚገነው የቲሬኖ ባሕር ሥር የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው የባሕር መናወጥ (tsunami)፣ አካባቢውን አጥፍቷል።
  • ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ከባሕር ሥር የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ሱማትራን ሲያወድም ያስከተለው የባሕር ሞገድ የኢንዶኔዚያን ጠቅላላ ጠረፍ አጥለቅልቆታል።
  • ፲፰፻፴፪ ዓ.ም. በሕንድ አገር ላይ የተነሳው ጥቅል አውሎንፋስ የኮሪንጋን ከተማ ሲያወድም፣ የተከተለው የውቅያኖስ ሞገድ ደግሞ ወደሃያ ሺህ የሚጠጉ መርከቦችን ጠራርጓል። ወደ ሦሥት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።
  • ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. በአሜሪካ ታሪክ ሃይለኛው የኅዳር ጥቅል አውሎንፋስ ተነስቶ በመካከለኛ - ምዕራባዊ ግዛቶች በጠቅላላው ሰባ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የጉዳቱ ብሶት በአርካንሳስ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ‘ሀርብ ስፕሪንግስ’ ላይ ሲሆን አምሣ አንዱ ሟቾች ከዚያው ግዛት ነበሩ።
  • ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. በሰሜናዊ ምሥራቅ አሜሪካ በሰዐት መቶ ስድሳ ኪሎሜትር ፍጥነት ያለው ንፋስ ያስከተለው የበረዶ ነበልባል የሦስት መቶ ሃያ ሦስት ሰዎች የሞት ምክንያት ሆኗል።
  • ፲፱፻፹ ዓ.ም. በሰዐት ሁለት መቶ ስድሳ አምስት ኪሎሜትር ፍጥነት ባለው ነፋስ የተነዳችው “ኒና”፣ (Super Typhoon Nina) የተባለችው አውሎንፋስ የፊሊፒን ደሴቶች ላይ የከሰተችው ቁጣ ወደ አንድ ሺህ ሠላሣ ሰዎችን ገድሏል።
  • ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የበረዶ ምታት በመካከለኛው የአሜሪካ ግዛቶች ላይ ሃያ ስድስት ሰዎችን ሲገል፤ በፍሎሪዳ ደግሞ በሰዐት መቶ አርባ አምሥት ኪሎሜትር ፍጥነት ያለው የነፋስ ምታት ተነስቶ ዛፎችን ፈነቃቀለ ሌላም ጉዳት አደረሰ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. በባኩ ኃይለኛ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ ሃያ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሌላ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. - በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ታላቁ ድርቅና ረሐብ እርዳታ እንዲሆን በብሪታንያ ሠላሣ ስድስት የሙዚቃ ባለሙያዎች “ባንድ ኤይድ” በሚል ስም ተሰባስበው፤ “የክርስቶስ ልደት መሆኑን ያውቁታል ወይ?” (Do They Know It's Christmas) የተባለውን ዘፈን ቀረጹ።
  • ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. - በአሜሪካ የ”ኢራን ኮንትራ አፌር” የተባለው የፖለቲካ ቅሌት ፈነዳ። ፕሬዚደንቱ ሮናልድ ሬጋን እና አቃቤ ሕጉ በስልጣን የነበሩ ሽርከኞች በምስጢር ለኢራን የጦር መሣሪያ እየሸጡ የሚገኘውን ትርፍ ደግሞ ለኒካራጓ ሽብርተኞች በምስጢር እንዳስተላለፉ ይፋ አደረጉ። ሁለት ባለሥልጣናት ወዲያው እንደተሻሩም ፕሬዚደንቱ ገለጹ።
  1. ^ Selected Speeches of His Imperial Majesty Haile Selassie I, 1918-1967 - page 522 –



የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ