ባኩ

ከውክፔዲያ

ባኩ (አዘርኛ፦ Bakı /ባኪ/) የአዘርባይጃን ዋና ከተማ ነው።

ባኩ ከ'ሳዱላ ግንብ' ሲታይ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 3 ሚሊዮን ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,074,300 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 40°22′ ሰሜን ኬክሮስ እና 49°53′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

'የሳዱላ ግንብ'፣ ባኩ

ባኩ እጅግ ጥንታዊ ነው። ከክ.በ. ምናልባት በ6ኛ ክፍለ ዘመን አንድ መቅደስ እዚህ ተሠራ። በአፈ ታሪክ ሃዋርያው በርተሎሜዎስ እዚህ የተቀበሩ ቢሆን ይህ ግን እርግጥኛ አይደለም። እስከ 8ኛ ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ድረስ ስሙ ባጋቫን እንደ ነበር ይታሥባል።


በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ባኩ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።