1945
Appearance
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1910ሮቹ 1920ዎቹ 1930ዎቹ - 1940ዎቹ - 1950ዎቹ 1960ዎቹ 1970ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1942 1943 1944 - 1945 - 1946 1947 1948 |
1945 አመተ ምኅረት
- መስከረም 8 ቀን - የሶቭየት ኅብረት ለጃፓን ዕጩነት በተመድ ውስጥ እምቢ አለች።
- መስከረም 28 ቀን - በ3 ባቡሮች ግጭት አድጋ በእንግሊዝ 112 ሰዎች ጠፉ።
- ጥቅምት 10 ቀን - በብሪታንያ ቅኝ ግዛት፣ ኬንያ ውስጥ ለነጻነት ይካሄድ የነበረውን የማው ማው ትግልን ለማክሸፍ በሚል ምክንያት የግዛቷ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው ኤቨሊን ቤሪንግ “አደገኛና አስቸኳይ ሁኔታ” አውጆ የሽብሩ መሪዎች የነበሩትን እነጆሞ ኬንያታን በእሥራት ቁጥጥር አዋለ።
- ጥቅምት 22 ቀን - አመሪካ መጀመርያ ሃይድሮጀን ቦምብ ፈተና በሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ አደረገ።
- ጥቅምት 25 ቀን - ድዋይት አይዘንሃወር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ አሸነፉ። (ጥር 12 ፕሬዚዳንት ሆኑ።)
- ጥር 23 ቀን - ታላቅ ጎርፍ በስሜን ባሕር 1835 ሰዎች በሆላንድና 307 በእንግሊዝ አጠፋ።
- የካቲት 26 ቀን - የሶቭየት ኅብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን ሞተ። (በሱ ፈንታ ኒኪታ ክሩሽቾቭ ተከተለ።)
- መጋቢት 9 ቀን - የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ 250 ሰዎች አጠፋ።
- ግንቦት 3 ቀን - አውሎ ንፋስ በቴክሳስ 114 ሰዎች ገደለ።
- ግንቦት 25 ቀን - 2 ኤልሳቤጥ የእንግሊዝ ንግሥት ሆነው ዘውድ ተጫኑ።
- ሰኔ 1 ቀን - አውሎ ንፋስ በሚሺጋን 115 ሰዎችና በማሣቹሰትስ 94 ሰዎች ገደለ።
- ሰኔ 11 ቀን - ግብጽ ሬፑብሊክ ሆነ።
- ሐምሌ 11 ቀን - በሆንዶ ደሴት ጃፓን 1700 ሰዎች በጎርፍ ሞቱ።
- ሐምሌ 20 ቀን - የኮርያ ጦርነት ጨረሰ።
- ነሐሴ 2 ቀን - የሶቭየት ኅብረት ደግሞ ሃይድሮጀን ቦምብ እንዳላት አዋጀች።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |