ጥቅምት ፲

ከውክፔዲያ
(ከጥቅምት 10 የተዛወረ)

ጥቅምት ፲

ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵ኛው እና የመፀው ፲፭ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፳፮ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፳፭ ዕለታት ይቀራሉ።


ዐቢይ ዓለም አቀፍ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፯፻፴፫ ዓ.ም “የአውስትሪያ አልጋ ውርስ ጦርነት” ዐቢይ ምክንያት የሚባለው፣ ንግሥትማሪያ ተሬዛ አባቷ ንጉሥ ቻርልስ ስድስተኛ በዛሬው ዕለት አርፎ እሷ ዙፋኑን መውረሷ ነው።
  • ፲፱፻፵፭ ዓ.ም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት፣ ኬንያ ውስጥ ለነጻነት ይካሄድ የነበረውን የማው ማው ትግልን ለማክሸፍ በሚል ምክንያት የግዛቷ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው ኤቨሊን ቤሪንግ “አደገኛና አስቸኳይ ሁኔታ” አውጆ የሽብሩ መሪዎች የነበሩትን እነጆሞ ኬንያታን በእሥራት ቁጥጥር አዋለ።

ልደቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. በ ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ሐረር ላይ ሰፍሮ ይኖር የነበረው፣ ፈረንሳዊው ግጥም ተቃኝ አርተር ራምቦ (Arthur Rimbaud)
  • ፲፰፻፹፬ ዓ.ም በጎረቤት አገር በኬንያ አገራቸውን ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻ ለማውጣት በመጋደል ቆይተው አገሪቱ ነጻ ስተውጣም የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የነበሩት ጆሞ ኬንያታ

ዕለተ ሙታን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፮፻፷ ዓ/ም - ጥቅምት ፲ ቀን ዋና ከተማቸው ጎንደር የነበረውና የጎንደርን ታዋቂ ቤተ መንግሥቶች የገነቡት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ፋሲል በተወለዱ በ፷፬ ዓመታቸው አረፉ።

ዋቢ መጻሕፍትና መረጃዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)ሰገላዊ አማርኛ፤ ፳፻ ዓ.ም


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ