መስከረም ፫
Appearance
መስከረም ፫ ቀን በየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫ኛ እና የክረምት ወቅት ፸፫ኛ ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፫፤ በ[ዘመነ ዮሐንስ]]፤ ዘመነ ማርቆስ እና በዘመነ ማቴዎስ ደግሞ ፫፻፷፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፫፻፸፫ ዓ/ም - የሩሲያ ኃያላት በኩሊኮቮ ውግያ የሞንጎልያን አደጋ አቆመ።
- ፲፰፻፵ ዓ/ም - አሜሪካውያን በሜክሲኮ ጦርነት ሜክሲኰ ከተማን ማረኩ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም - ሳልስበሪ፣ ሮዴዚያ ተመሰረተች።
- ፲፰፻፺፫ ዓ/ም - በፊሊፒንስ ጦርነት የፊሊፒንስ ተዋጊዎች በአሜሪካ ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ።
- ፲፰፻፺፱ ዓ/ም - በአውሮፓ የተደረገ መጀመርያው የአውሮፕላን በረራ።
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች የቀድሞዋን ጀርመን-ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ (አሁን ናሚቢያ) ወረሩ።
- ፲፱፻፲፬ ዓ/ም - ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በዚህ ዕለት ተቋቋመ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ኅብረት መንኮራኩር ጨረቃ በመድረስ የመጀመሪያው ኾነ ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - ኪሪባስ፣ ናውሩ እና ቶንጋ ደሴቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባላት ኾኑ።
- ፲፱፻፺፮ ዓ/ም - የስዊድን ሕዝብ የአውሮፓ ኅብረትን ገንዘብ (ዩሮ) ለመቀላቀል ወይም ላለመቀላቀል በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) በአብላጫ ድምጽ ላለመቀላቅል ወሰነ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |