አቴና
Appearance

አቴና (ግሪክኛ፦ Αθήνα /አጤና/) የግሪክ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 3,247,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 747,300 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 38°00′ ሰሜን ኬክሮስ እና 23°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
በጥንታዊ ግሪክና እስከ 1968 ዓ.ም. ድረስ የከተማው ግሪክኛ ስም በይፋ «አጤናይ» ነበረ። በዚያው ዓመት ዘመናዊው ግሪም ስም አጤና ይፋዊ ሁኔታ አገኘ።
| ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |