የካቲት ፳
Appearance
የካቲት ፳፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፸ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፭ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፺፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፭ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፸፪ ዓ/ም - በኢራን የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ ፪ መቶ ሺህ ሰዎችን አጠፋ።
- ፲፰፻፹፱ ዓ/ም - በማዳጋስካር፣ የፈረንሳይ የጦር ኃይል ሳልሳዊት ንግሥት ራናቫሎናን ከሥልጣን ሲያወርድ በማዳጋስካር የዘውድ ሥርዓት አከተመ።
- ፲፱፻፲፬ ዓ/ም - የብሪታኒያ ንጉዛት መንግሥት በራሱ ፈቃድ በግብጽ ላይ የነበረውን ሉዐላዊነት አቁሞ ነጻነትን ለግብጻውያን አሳልፎ ሲሰጥ የውጭ ጉዳይን፤ ግንኙነትን፤ የጦር ሠራዊትንና የግብጽ ሱዳንን አስተዳደር የሚመለከቱ ጉዳዮችን ግን በራሱ አስተዳደር ሥር አስቀረ።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - ለዱፖንት ኩባንያ ይሠራ የነበረው ዋላስ ካሮዘርስ ናይሎን (Nylon) ፈጠረ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ፍንዳታ፣ የወታደሩ አመጽ ተስፋፍቶ አዲስ አበባ የሚገኙ የ፬ ኛ ክፍለ ጦር፤ የጦር ሠራዊት፤ ዓየር ኃይል እና የዋና መሥሪያ ቤት ወታደሮች በከተማው ‘ቁልፍ’ ቦታዎችን በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ። ብዙዎችን የአክሊሉ ሀብተ-ወልድን ሚኒስቴሮች አስረው ያዙ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አቶ እንዳልካቸው መኮንንን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እና ጄኔራል አቢይ አበበን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ ሊካሄድ ተዘጋጅቶ የነበረው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ስብሰባ በረብሻው ምክንያት ተሰረዘ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የመሬት እንቅጥቅጥ በአርሜኒያ እና አዘርባይጃን አገሮች ፩ ሺህ ፩ መቶ ሰዎች ሲገል፣ በሰሜን ኢራን ደግሞ ፫ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |