መስከረም ፭
Appearance
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፭ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፷ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም -አጼ ልብነ ድንግል በነገሡ በ፴፪ ዓመታቸው ሐሙስ ዕለትደብረ ዳሞ ላይ አረፉ። የንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን፣ ዘውድና ዙፋናቸው በዚሁ ዕለት ወደልጃቸው የ ፲፰ ዓመቱ አጼ ገላውዴዎስ (ስመ መንግሥት፣ አፅራር ሰገድ)ተላለፈ።
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ ታንክ የተባለው የጦር መሣሪያ አገልግሎት ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራና ኢትዮጵያ በ”ኅብረታዊ መንግሥት” እንዲዋሃዱ አጸደቀ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - በሁለት ትላልቅ የኢትዮጵያሕዝባዊ ድርጅቶች የመሪዎች መፈንቅል ተፈጸመ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት ስድስት ዓመት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ ሥራቸውን ለቀቁ። አቶ ግርማን የሚተኳቸው ምክትላቸው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይሆናሉ ይባላል። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አማረ አምሳሉም ሥራቸውን ለቀቁ
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም በወንጀላዊ ልብ ወለድ ጽሑፎቿ “አቻ የላት” የምትባለው እንግሊዛዊቷ ደራሲ አጋታ ክሪስቲ (Agatha Christie)፣ ቶርኪ (Torquay) በምትባል ከተማ ተወለደች። (ክሪስቲ በ ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሞተች)
- * መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ "የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |