ኖቤል ሽልማት
Appearance
የኖቤል ሽልማቶች ከ1893 ዓም ጀምሮ በስዊድን ሳይንቲስት አልፍሬድ ኖቤል ስም በየዓመቱ የሚሰጡ ታላቅ ስልማቶች ናቸው። አልፍሬድ ኖቤል በኑዛዜው በገዛ ሀብቱ የሽልማቱን ሥርዓት መሠረተ። ሽልማቶቹ በሚከተሉት መደቦች ይሠጣሉ።
- የኖቤል ሽልማት በፊዚክስ
- የኖቤል ሽልማት በኬሚስትሪ
- የኖቤል ሽልማት በሕክምና
- የኖቤል ሽልማት በሥነ ጽሑፍ
- (ከ1961 ዓም ጀምሮ) የኖቤል ሽልማት በምጣኔ ሀብት (በይፋ «የስዊድን ባንክ ሽልማት በምጣኔ ሀብት» ይባላል)
- የኖቤል ሰላም ሽልማት
የኖቤል ሰላም ሽልማት በኖርዌይ ምክር ቤት ጉባኤ ይወሰናል። ሌሎቹ ሽልማቶቹ በስዊድን ተቋማት ይወሰናሉ።
ከወርቃማው ሽልማት በላይ ተቀባዮች አንድ ሚሊዮን ዶላር ያህል ያገኛሉ።