ጥቅምት ፲፫
Appearance
ጥቅምት ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፫ኛው እና የመፀው ፲፰ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፫ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳፪ ቀናት ይቀራሉ።
በሁንጋሪያ በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም ተነስቶ የነበረውን ጸረ ስታሊን ሽብር እና አዲሲቱ የሁንጋሪያ ሪፑብሊክ በ ፲፱፻፹፪ ዓ.ም በአገሪቱ ፕሬዚደንት ማትያስ ስዙሮስ የታወጀበት ዕለት ማስታወሻ የብሔራዊ ቀን ነው።
- ፲፱፻፬ ዓ/ም - በቱርክና በኢጣሊያ መካከል በነበረው ጦርነት የቱርኮችን የጦር ግንባር ከአየር ለመሰለል የኢጣልያ አውሮፕላን ከሊቢያ ተነሳ። ይሄም ድርጊት አውሮፕላን በጦርነት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለበት ዕለት ነው።
- ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ፔሌ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የብራዚል እግር ኳስ ተጫውች ኤዲሶን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ተወለደ። ፔሌ በዓለም የኦሊምፒክ ሸምቡድ[1] (International Olympic Committee) “የ፳ኛው ክፍለ ዘመን አትሌት” ብሎታል።
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - ግብጻዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ አርፈው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)፣ "ሰገላዊ አማርኛ፤ ፳፻ ዓ.ም
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/165300 Ethiopia: Annual Review of 1961
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |