Jump to content

መስከረም ፲፱

ከውክፔዲያ

መስከረም ፲፱

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፱ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፫፻፵፯ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፫፻፵፮ ዕለታት ይቀራሉ።


፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት አገራችንን ኢትዮጵያን ሲወር በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገባው ማርሻል ፒዬትሮ ባዶልዮ፤ ተሸናፊዋን አገሩን በመወከል የሽንፈቱን ስምምነት ፈረመ።

፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ከዚያ በፊት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ በ ሶቪዬት ኅብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቾቭ ድንፋታ ተረበሸ። በዚህ ስብሰባ ላይ ክሩስቾቭ ጫማቸውን አውልቀው ጠረጴዛቸውን በመቀጥቀጥ ዓለምን አስገርመዋታል።

፳፻፪ ዓ/ም - በሳሞዓ አጥቢያ የተከሰተው፣ በ ‘ሪክተር ሚዛን’ ስምንት ነጥብ ያስመዘገበው የመሬት እንቅጥቅጥ ‘ሱናሚ’ (tsunami) የሚባለውን የባሕር ነውጥ አስከተለ።




የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ