ግራኝ አህመድ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

በተለምዶው ግራኝ አህመድ ተብሎ የሚታወቀው የጦር መሪና የኢትዮፕያ ንጉስ ሙሉ ስሙ ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ሲሆን የኖረውም ከ1507 እስክ ታህሳስ 21፣ 1543 (እ.ኤ.አ) ነበር። [1]) በዘመኑ በእስልምና ሃይማኖት የኢማምነት ደረጃ የደረሰ ሲሆን የአዳል ግዛት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የጥንቱን የኢትዮጵያ ክፍል በመምራት እንዲሁም በዘመኑ የነበሩትን ነገስታት ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንዲያፈገፍጉ በማድረግ በታሪክ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ 3/4ኛ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ክፍል ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችሏል። [1] አንድ አንድ የታሪክ ተመራማሪዎችም የግራኝ አህመድ ሰራዊት ከሞላ ጎደል በሱማሌ ጎሳ ሰዎች የተድሎችን በመቀዳጀቱ ምክኒያት በዚህ ስያሜ እንደጠሩት ይነገራል። ይህ መሪ ከ1529 እስከ 1543 ከነበሩት የመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነገስታት ጋር ጦርነት እንዳረገ ታሪክ ይዘግባል።[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የግራኝ አህመድ ጎሳ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

d͡ʑ ጻህፍት ዘንድ እንደሚታመነው ግራኝ አረብ እንደነበር ሲሆን[2] በሌሎች ታሪክ ተመራማሪወች ዘንድ ግን ሱማሌ እንደሆነ ነው።[1][2][3][4][5][6][7][8][9] እንደ እስራኤላዊው የታሪክ ተመራማሪ ሃጋይ ኽልሪች ግን ግራኝ አህመድ ሱማሊኛ ቋንቋን እንደማይናገር አትቷል። [10] በሌላ ሁኔታ ብዙ የታሪክ ጸሃፍት እና መረጃዎች ግራኝ አህመድ የሐረር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሰዋል::[11][12][13][14][15][16]

ለግራኝ አህመድ እንቅስቃሴ አስተዋጾ ያደረጉ ነገዶች እንደ ኢሳቅዳሩድ እና ማረሃን የተሰኙት የሱማሌ ጎሳወች ሲሆኑ ጎሳወቹ ግን በዘር ምክንያት ሳይሆን ያብሩ የነበሩት በሃይማኖት ተመሳሳይነት ነበር። [17]

ብሶት የወለደው ጀግና[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ብሶት አንዳንዴ ለታላቅ ዓላማ መነሻ ይሆናል። በኢማም አሕመድ ኢብኑ ኢብራሂም አልጋዚ ላይ የታየውም ይሄ ነው።

ኢማም አሕመድ በ1506 ሁበት በተባለ በልዩ ስሙም ዘዕካ በሚሰኝና ጋሪ ሙለታ እየተባለ ከሚጠራው ተራራ አቅራቢያ በምትገኘው ከሀረርም 32 ኪ.ሜ በምትርቀው ቦታ ተወልደው 10 ዓመት እንደሞላቸው ነበር በአዳል ሥርወ መንግስት መሪነት ለ25 ዓመታት ለሙስሊሙ ሲታገል የኖረው ኢማም ማሕፉዝ የተገደለው።

መቼም በትንሹ የገራድ አሕመድ ልብ ውስጥ በነፃ አውጪነት ሲታወቅ የነበረው በቅርብ የሚታወቀው ኢማም ማሕፉዝ ሲሞት ያውም በልብነ ድንግል ሰራዊት አንገቱ ተቆርጦ መወሰዱ ከፍተኛ ሀዘን ይፈጥራል።

ገራድ አሕመድ ሲያድግም በአባቱ ነፃ አውጪ አድሊ የተባለ ሰው እጅ ነበርና በገራድ አሕመድ ስብዕና ላይ የአድሊ ተፅዕኖ ላቅ ያለ ነበር። በወቅቱ የኢማም ማሕፉዝን መሞት ተከትሎ የተንሰራፋውን ስርዐት አልበኝነትና የተዳከመችውን የአዳል ሱልጣኔት ለማረጋጋት ገራድ አቡን የተባለ ታጋይ ይንቀሳቀስ ነበር። በስሩም ብዙ ፈረሰኞችና እግረኛ የጦር ሰራዊት አባላት ነበሩት።

ወጣቱ ገራድ አሕመድም የመጀመሪያውን የትግል ምዕራፍ ከገራድ አቡን ጋር ፈረሰኛ ሆኖ በመሰለፍ ጀመረ። ገራድ አቡንም የቆፍጣናውን ወጣት አሕመድን ቅልጥፍናና ብልሀት እንዲሁም አርቆ አሳቢነት ስለተገነዘበ የቅርብ ሰው አደረገው።

ወጣቱ ገራድ አሕመድ ከገራድ አቡን ጋር ተሰልፏል። በዚያው ወቅት ደካር ከተባለችው ቦታ የነበረው ሱልጣን አቡበከር የአዳልን መቀመጫ ከተማ ወደ ሐረር አዞረ። እናም በሱልጧን አቡበክር አገዛዝ ኢስላማዊ ያልሆኑ ባህሎች መንሰራፋት ጀመሩ። መጠጥና ቁማርም እየተለመደ መጣ ሽፍቶችም በዙ።

በዚህ ጊዜ ይህ ሁኔታ ያበሳጨው የነ ገራድ አሕመድ አለቃ በአካባቢው ይታይ የነበረው መጥፎ ገፅታ ለማጥፋት አዋጅ አስነገረ። ቁማርና መጠጥንም አገደ ሽፍታም አሳደደ። ታድያ በዚህ ጊዜ የገራድ አካሄድ ያልተመቸው ሱልጣን አቄመበት። ሗላም በሜይ 30 1525 ሱልጣን ገራድ አቡንን ሽፍታ ቀጥሮ አስገደለው።

በገራድ ቁጥጥር ሥር የነበሩ መንደሮችም ወደ ሱልጣኑ ግዛት ተካተቱ። የገራድ ጎበዞችም ተበተኑ። በሀገሪቱም ሽፍታዎች ተመለሱ ቁማርና መጠጥም ተንሰራፋ ቀማኞች በዙ ፍትህም ጠፋ። ሱልጣን አቡበክርም በአካባቢው ሽማግሌዎችና መሻይኾች ቢመከርም አልሰማም አለ። ያኔ ነው እንግዲህ በሱልጣን ስም ብልሹነት መነዛቱ ያበሳጨውና የጋራ ጠላት እያለ የወዳጁ ሞት ያተከነው ፣ የኢስላምና ሸሪዓ መደፈር ያቆሰለው ገራድ አሕመድ ቢን ገራድ ኢብራሂም የኃላው ኢማም አሕመድ በብሶትና ቁጭት ወደ ትውልድ መንደሩ ሁበት ተጉዞ ሰራዊት መመልመልና ማዘጋጀት የጀመረው።

በዚያ በኩል የልብነ ድንግል ክፉ ጦር ሙስሊሞችን በየቦታው እየረፈረፈ በዚህ በኩል ለሙስሊሞች የቆመን ታጋይ የሚገድለው ሌላ ሙስሊም ጡንቸኛ መሆኑ ያቆስላል። ከስልጣንና ገንዘብ ይልቅ አንድ ያደረጋቸው እስልምና መመረጥ ሲገባው አላግባብ የሆነ ሂደት መኬዱ ያተክናል። ለዚያ ነው ኢማም አሕመድ ሸሪዓ የማያከብር፣ ለገንዘብ ያደረ፣ ስልጣን የጠማው፣ ነፃነት የማያውቀውን ሰው አስወግዶ መላውን ሙስሊም በአንድ ጥላ ስር አሰልፎ ክብሩን ለመጠበቅ የወሰነው። ሁበትም የገዛ ውልዷን እንኳን ደህና መጣህ ብላ በሆታ ተቀበለች።


[[==ዘመቻ ፋኑኤል==


ገራድ አሕመድ በሱልጣን አቡበክር አስተዳደር ስር የሚያየው ሥርአት አልበኝነት አናዶታል ሸሪአን ባለመጠበቁና ቁርዐን እና ሀዲስ መደፈሩም አበሳጭቶታል። በዚህም የተነሳ ወደ ትውልድ ሀገሩ ሆባት ተጉዞ ጦር ማደራጀት ጀመረ በዚህም ከመቶ በላይ ፈረሰኛ ጦር በስሩ ተሰለፈ። ኢማም የሚለውን ማዕረግም በዛው አገኘ። እስካሁን ገራድ ያልኩት ሹም በሰራዊቱ ኢማም ተብሎ መጠራት በመጀመሩ ከዚህ በኃላ እኔም ኢማም ስል እጠራዋለሁ።

ኢማሙ አሕመድ በዛው ሰራዊት በሚመለምልበት ወቅት በወጣትነቱ እንደ አርዓያ ያየው የነበረውና በ10 አመቱ የተገደለውን የገራድ ማሕፉዝን ልጅ ባቲ ድል ወንበሯን አገባ። ድል ወንበሯ የማዕረግ ስሟ ሲሆን ከአባቷ ዘመን ጀምሮ በጦር ቀጥታ ተሳታፊነቷ ብሎም ድል ወይም ማሸነፍን እንደ ወንበሯ ስለተደላደለችበት የተሰጣት ስም ነው። ይህቺ ሴት ዓለም ከሚያውቃቸው ጥቂት ጀግናና ብልህ ንግስቶችና የጦር አለቃ ሚስቶች መካከል አንዷ ናት። ወደፊት ሚናዋን የምንመጣበት ይሆናል።

የሆነ ሆነና ብርቱ የሴት ደጀን ያገኘው ኢማም በልጅነቱ ከገራድ አቡን ጋር ተሰልፎ የተማረው የወታደር ዲሲፒሊንና ያካበተው የጦር ስልትና ጥንካሬ ጠቅሞትም በመላው ሆባት ዝናው ናኘ። በሐረርም ዝናው መነዛት መጀመሩ ሱልጣን አቡበከርን ስጋት ውስጥ ከተተው። በዚህ ማሀል ፋኑኤል የሚባል የደዋሮ ገዢ የነበረ ቄስ ሰራዊት አስከትሎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በሚያደርገው ጉዞ በሁበት ሲያልፍ በማን አለብኝነት ወታደሮቹ ሙስሊሞችን እንዲያጠቁ አዘዘ። ሰራዊቱም ህዝቡን አጠቃ በሀገሪቱ ጩኸት ነገሰ። ሙስሊሞች ተገደሉ። ቤቶች ተቃጠሉ። ሴቶችና ህፃናትም በወታደሮቹ ተያዙና ጉዞው ቀጠለ። ይህ ተግባር በዚያን ጊዜ የተለመደ ነበር። ሙስሊሞች ላይ የበሬ ግንባር የምታህል ቀዬ አስተዳደሪ ሁሉ ይጎረምስ ነበር። ኢማሙ በሁበት አቅራቢያ በከተሙበት በዚያ ወቅት ግን ይህ ግፍ ሊቆም እንደሆነ ታየ።

በሁበት አቅራቢያ የነበረው ኢማም አሕመድም የፋኑኤልን ድርጊት ሰማ። በግዜው ነገስታት የሚተዳደሩ ሃገሮች ላይ ይህ ክስተት የሚያስደንቅ ባይሆንም በሱልጣን አቡ በክር ግዛት ውስጥ ሙስሊሞች በማን አለብኝነት ሲደፈሩና ሲገደሉ ማየትና መስማት እጅግ ያቆስላል። ይህም ኢማሙን አቆሰለ። ከንፈር ያስነከሰው ደግሞ በፋኑኤል ብቻ ሳይሆን በሱልጣኑም ላይ ነበር። ወሬ ነጋሪው ለኢማሙ ፋኑኤል ከዘረፈው ንብረት ሌላ ሴትና ህፃናት እንደወሰደም ነገራቸው። ያኔ ኢማሙ ተቆጡ። ክተት ሰራዊት፣ ምታ ነጋሪት አሉ። ሰራዊታቸውን አሰባስበውም ወደ ፋኑኤል ዘመቱ። በጉዟቸው ላይ የነበራቸው ቆራጥነት ግን ለመጀመርያ ጊዜ ሳይሆን ለ100ኛ ጊዜ ጦርነት እየመሩ ይመስል ነበር። በጊዜው ኢማሙ ገና የ21 ዓመት ወጣት ቢሆኑም ቁጣቸው ወኔያቸው እቅዳቸው አስደናቂ ነበር።

የኢማሙና የፋኑኤል ጦርም ዓቂም (አማሬሳ) ወንዝ ጋር ተገናኙ። በመካከላቸውም ከፍተኛ ጦርነት ተካሄደ። ከፊሉ የኢማሙ ጦር በግራ በኩል በፋኑኤል ጦር ላይ ጥቃት ሲከፍት ኢማሙ በመሀል በኩል ዘልቆ የፋኑኤልን ጦር ያተራምሰው ገባ። በኋላም በርካታ የፋኑኤል አበጋዞችና ባላባቶች ተገደሉ። የተወሰዱ ህፃናትና ሴቶችም ተለቀቁ። ጦርነቱም በድል አድራጊነት ተጠናቀቀ። ከፋኑኤል ወገን በርካታ ሰው ተገድሎ 60 ፈረሰኞችና ብዛት ያላቸው እግረኛች ተማርከው እጅግ ብዙ የጦር መሳርያም አብሮ ተማርከ።

ኢማሙ ካስለቀቋቸው ሙስሊም ሴቶችና ህፃናት ፣ የተማረኩ ወታደሮችና መሳሪያዎች ጋር በድል አድራጊነት ወደ ዚፋህ ከተማ ገቡ። የመጀመርያ ጦርነታቸውንም በድል ተወጡ። ኢማሙ የእግር እሳት የሆኑበት ሱልጣን አቡበክር የኢማሙን ድል እና ያገኘውን ምርኮ ሲሰማ ኢማሙ ወደሱ መዝመታቸው አለመቅረቱን ስለተረዳ ሐረርን ለቆ ወደ ሶማሊያ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሸሸ። ወትሮም ለወገኑ መሟገት ያልቻለ መስፍን መወቃቱ የማይቀር መሆኑን ኢማሙም አሳምረው የውቃሉ።]]

የኢማሙ ዳግም ድል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢማሙን በ18 ዓመት እድሜ የተገኘ ድል ሰምቶና ደንግጦ መናገሻ ከተማውን ሀረርን ጥሎ ወደ ሶማሊያ የሸሸው ሱልጣን አቡበክር ኪዳር (ኪዳድ) በምትባል ቦታ ተደበቀ።

ኢማሙም በነካ እጁ በሙስሊሙ መካከል ፈሳድ እንዲስፋፋና ሙስሊሙ የአንድነት ሀይልና ወኔው እንዲነጥፍ ምክነያት የሆነውን ሱልጣን አቡበክር ለማጥቃት ወደተደበቀበት ከተማ ተጓዘ። ኢማሙ ቦታው ላይ ሲደርሱም ሱልጣኑ ጦሩን አሰልፎ ጠበቃቸው። ሁለቱ ጦሮችም ዝሁር ወቅት ላይ ተገናኙ ኢማሙና ጓዶቻቸውም በኢስላማዊ ህብረትና ሙሐመዳዊ ወኔ ማጥቃት ጀመሩ። በርካታው የሱልጣኑ ሰራዊት ተገደለ። ከፊሉም ሱልጣኑን ጨምሮ ሸሸ።

ኢማሙ 20 አመት ሳይሞላቸው ሁለተኛውን ጦርነታቸውን በፍፁም ድል አድራጊነት ተወጡ። የሱልጣኑን መሸሸጊያ አወደሙ። በዚህ ጦርነትም ኢማሙ 30 ፈረስና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማረኩ። ነገር ግን ኢማሙ ሐረር ገብተው ብዙ ሳይቆዩ ሱልጣኑ ለቁጥር የሚያዳግት ሰራዊት እዛው ሶማሌያ ላይ ሰበሰበና ኢማሙን ለማጥቃት ወደ ሐረር ተመመ።

የሱልጣኑ ጦር በርካታ ፈረሰኞችን ያካተተ ስለነበር ኢማሙ የሱልጣኑን መቃረብ ሲሰሙ ስልታዊ ማፈግፈግን መረጡ። ከነጦራቸውም ወደ ሁበት ተጉዘው ጋረሙለታ ተራራ ላይ መሸጉ። ሱልጣኑም ሐረር ገባ።

ኢማም አሕመድ በጋሪሙለታ ተራራ ላይ መስፈራቸውን የሰማው ሱልጣን ጦሩን ይዞ ሁበት ገባ። ተራራውንም ለቁጥር ባዳገተው ሰራዊት አስከበበው። ከፍተኛ ጥበቃም አደረገ። የኢማሙ ጦር ከተራራው መውረድና ለህይወት መሠረታዊ የሆኑትን ምግብና የመጠጥ ውሀ ማግኘት አልቻሉም። ሱልጣኑ በዚህ ሁኔታ ለሁለት ሳምንታት ያህል ከበባውን አጠናክሮ ቀጠለ። በስተመጨረሻ ግን የኢማሙ ጦር ተዳከመና ተስፋ መቁረጥ ታየ። ስለሆነም በለሊት የኢማሙ ጦር ወርዶ ከሱልጣኑ ጋር ጦርነት ገጠሙ። ዳሩ ግን የኢማሙ ጦር ለ2 ሳምንት ታግቶ የቆየ በመሆኑ ውጊያው ላይ ቀልጣፋ መሆን አልቻለም። በመሆኑም የኢማሙ ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃ።

ከአንጋፋ የኢማሙ የጦር አዝማቾች መካከል አንዱ ዑመረዲንም ተገደለ። ኢማሙና ጥቂት ጓዶቻቸው ግን አመለጡ። የኋላ ኋላ ግን በዘመኑ ዑለማኦች ከፍተኛ ጥረት በሁለቱ አሚሮች መካከል ስምምነት እንዲኖር ተደረገ። ስምምነቱም ሱልጣኑ ሸሪዓን ሊጠብቅና በፍትህ ሊያስተዳድር ኢማሙና ጦራቸው ደግሞ መሸፈቱን አቁሞ ለሱልጣኑ ታዛዥ ሆኖ በሰላም እንዲኖር የሚያግባባ ነበር። ስምምነቱም መተግበር ተጀመረ። ኢማሙም ጥማታቸው የስልጣን ሳይሆን የሸሪዓ መጠበቅ መሆኑን ሰጥ ለጥ ብለው ለሱልጣኑ በመታዘዝ አሳዩ። በኋላ ግን ሱልጣኑ ስምምነቱን አፈረሰ።

ቀደምት አመታት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኢማም ግራኝ አህመድ የተወለደው ዘይላ ተብላ ትታወቅ በነበረው የባህር በር አካባቢ በሰሜናዊ ምዕራብ አዳል ( በአሁኑ ዘመን ሶማሊያ) ነበር።

የአዳል ሱልጣኔት

ይህ ታሪካዊ አዳል (ሶማሊያ) የእስልምና ሃይማኖትን የሚከተል መንግስት ይሁን እንጂ በጊዜ ለነበረ የክርስትና ተከታይ ኢትዮጵያው መካከለኛ መንግስት ግብር ይከፍል ነበር። ግራኝም በጎለመሰ ጊዜ ማህፉዝ የተባለን የዘይላ አስተዳዳሪን ልጅ ባቲ ድል ወምበሬ አገባ።.[6]

ድል ወምበሬ

ነገር ግን ማህፉዝ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ተጣልቶ በአጼ ልብነ ድንግል ላይ ጥቃት አድርሶ ሲመለስ በ1517 ተገደለ። በአዳል እርስ በርስ ጦርነት ተነሳ። ግራኝ አህመድም ከተወሰኑ የትግል ዓመታት በኋላ በስልጣን የሚሻኮቱትን በማሸነፍ ሐረርን ተቆጣጠረ። በዚህ ጊዜ የአዳል መሪ ሆነ።

ዘመቻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1527፣ የአዳል መሪ ከሆነ በኋላ፣ ከአዳል ከትሞች የሚጠበቀውን ግብር ለመካከለኛው የኢትዮጵያ መንገስት እንዳይከፈል አገደ። አጼ ልብነ ድንግልም የባሌ ጦር አዛዡን ደግላን ግብሩን እንዲያስከፍል ላከ። ደግላን ግን በአዲር ጦርነት ተሸነፈ። ከዚህ ቀጥሎ ግራኝ ወደ ምስራቅ በመዝመት ሱማሌውችን በጦርነት ግዛቱ አደረገ። ቀስ ብሎም ወደ ምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ብዙ ዘመቻወችን በማካሄድ ስፍር ቁጥር የሌላችቸው ባሪያወችን በመፈንገል በደቡብ አረቢያ፣ ለዘቢድ አስተዳዳሪ በስጦታ መልክ በመላክ በተራው የብዙ ጠመንጃወች ባለቤት ሆነ። [18] በ1528 የልብነ ድንግል ሰራዊት በአዳል ላይ ጥቃት ስላደረሰ፣ ይህን ለመበቀል በ1529 በክርስትያኑ ንጉስ ላይ ኢማም አህመድ ዘመቻውን የኢትዮጵያና አዳል ጦርነት ጀመረ። መሰረታዊው የኢማም አህመድ አላማ ግን "ጅሃድ" ወይም "በሃይማኖት መታገል" ነበር [19] ። በዚህ ጊዜ የአጼ ልብነ ድንግልን ሰራዊት መምጣት የሰሙት የግራኝ ወታደሮች በፍርሃት ተውጠው ለመሸሽ ሲሞክሩ፣ ግራኝ ግን በጽናትና ቆራጥነት አብዛኞቹ ባሉበት እንዲቆሙ በማድረግ የልብነ ድንግልን ሰራዊት ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኘው በሽምብራ ቁሬ ጦርነት መጋቢት 1529 አሸነፈ[20]ጦርነቱን ያሸንፍ እንጂ ብዙ ወታደሮች ስላለቁበት ቀሪው ሰራዊቱ ወደሃገሩ ተመልሶ ከንደገና መታገል ሰጋ። በዚህ መሃል ከአረብ አገር 70 ሙሉ ትጥቅ ያላቸው ወታደሮችና ብዙ ጠብመንጃወች እና 7 መድፎች ከኦቶማን ቱርኮች አገኘ። በ1531፣ የግራኝ ጦር የልብነ ድንግልን ሰራዊት አምባሰል አንጾኪያ ላይ ገጥሞ እንደገና ድል አደረገ። ለዚህ ድል መሰረቱ በዕርዳታ ያገኘው መድፍ እንደነበር ሉዶልፍ ሲያትት ከግራኝ ወገን የተተኮሰ መድፍ ጥይት በአጋጣሚ ልብነ ድንግል ሰራዊት መካከል ወደቀ፣ ይህ እንግዳ መሳሪያ የሚያሰክትለውን ቁስል እንኳ እንዴት ማዳን እንደሚቻል የማያውቁጥ ኢትዮጵያውያን በድንጋጤ ተበታተኑ [21]። ከዚህ በኋላ የኢማሙ ሰራዊት ወደሰሜን በመዝመት በሃይቅ፣ ወሎ ደሴቶች ላይ የነበሩትን አካባቢዎችን ተቆጣጠረ። ቀጥሎም ትግራይ ውስጥ ይጠብቀው የነበረውን ሰራዊት በማሸነፍ አክሱም ከተማ ተቆጣጠረ።

ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድማ ንግስት እሌኒ የተባለችው የሃድያ ንግስት ( የዘርዓ ያዕቆብ ሚስት)፣ ለፖርቱጋሎች የወታደር እርዳታ እንዲያረጉ መልዕክት ልካ ኖሮ፣ ታህሳስ 10፣ 1541 400 ጠመንጃ ያነገቱ የፕርቱጋል ሰራዊት ምጽዋ ላይ አረፉ። በዚህ ጊዜ አጼ ልብነ ድንግል በስደት እያለ በ1540 ሲሞት እሱን ተክቶ አጼ ገላውዲወስ ንጉሰ ነገስት ሆኖ ነበር። በ ክሪስታቮ ደጋማ የሚመራው የፖርቹጋሎቹ ሰራዊትና ኢትዮጵያውያን ሚያዚያ 1፣ 1542 በጃርቴ ጦርነት (ጃርቴ በሌላ ስሙ አናሳ ሲባል በአምባላጌ እና በአሻንጌ ሃይቅ መካከል የሚገኝ ቦታ ነው) ከ ግራኝ ሰራዊት ጋር የመጀምሪያ ፍልሚያ አደረገ። በዚህ ጊዜ ፖርቱጋሎቹ ግራኝን ለመጀመሪያ ጊዜ ማየታቸው ሲሆን በጊዜው የነበረው ፖርቹጋላዊው ካስታንሶ ክሩቅ ሆኖ ስላየው ስለግራኝ እንዲህ ይላል፦

በሱ በኩል ያለውን የጦር አውድማ በሚዘጋጅበት ጊዜ፣ የዘይላው ንጉስ ኢማም አህመድ ኮረብታው ላይ ወጣ። በዚህ ጊዜ ብዙ ፈረሰኞች አብረው ተከትለውት ነበር፣ እግረኞችም እንዲሁ። የእኛን የጦር ቀጠና ለመመርመር፣ እኮረብታው ጫፍ ሲደረስ ከ300 ፈረሶች እና ሶስት ግዙፍ ባንዲራወች ጋር ቆመ። አርማዎቹም ሁለቱ ነጭና መካከላቸው ላይ ቀይ ጨረቃ ምልክት ሲኖራቸው አንዱ ደግሞ ቀይና መሃሉ ላይ ነጭ ጨረቃ ያሉባቸው ከንጉሱ ዘንድ ምንጊዜም የማይለዩ ነበሩ ይላል። [22]

በዚህ ሁኔታ ለ4 ቀናት በመፋጠጥና መልዕክት በመለዋወጥ እኒህ የማይተዋወቁ ሁለት ሰራዊት ጊዜያቸውን ካሳለፉ በኋላ ክሪስታቮ ደጋማ እግረኛ ወታደሮቹን (ኢትዮጵያኖችንም ይጨምራል) በአራት ማዕዘን ቅርጽ በማደራጀት ወደ ኢማሙ ሰራዊት ዘመተ። የእስላሙ ሰራዊት፣ ብዙ ጊዜ እየደጋገመ ጥቃት ቢያደረስም በመድፍና በጠመንጃ የታጠረ አራት ማዕዘኑ ሊሸነፍ አልቻለም። በዚህ ጦርነት መካከል በድንገት በተተኮሰ ጥይት ግራኝ አህመድ እግሩ ላይ ቆሰለ። ስለሆነም የኢማሙ ሰራዊት መሸሽ መጀመሩን ያዩት የኢትዮጵያና የፖርቹጋል ሰራዊት ተበታትኖ የሚሮጠውን ሰራዊት በማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ። ይሁንና የቀሩት ወታደሮች ከእንደገና በማደራጀት ኢማሙ ጦርነት ከተካሄደብት ወንዝ ራቅ ብሎ ሰፈረ።

በሚቀጥሉት ጥቂት የግራኙ ጎራ አዳዲስ ወታደሮች በማስመጣት በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከር ጀመረ። ይህ ነገር ያላማረው ደጋማ ቶሎ ብሎ ጦርነት መግጠም አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ መጋቢት 16 ላይ አሁንም አራት ማዕዘን በመስራት ዘመተ። ምንም እንኳ የኢማሙ ጦር ከበፊቱ በበለጠ ቁርጠኝነት ቢዋጉም፣ በድንገት በፈነዳ የጥይት ቀልህ ምክንያት ፈረሶቹ በመደናገጣቸው አራቱ ማዕዘን አሁንም አሸነፈ። በዚህ ጊዜ የኢማሙ ሰራዊት በዕውር ደንብስ እያመለጠ ሸሸ። ክሳታንሶ የተባለው ፖርቱጋላዊም በጸጸት እንዲህ ብሎ መዘገበ፡

መቶ የሚሆኑ ፈረሶች ቢኖሩን ኑሮ የዛሬው ቀን ድል የተሟላ ይሆን ነበረ ምክንያቱም ንጉሱ እራሱ በቃሬዛ አራት ሰወች ተሸክመውት ነው ያመለጠው። ቀሪው ሰራዊትም የሸሸው በተረጋጋ ሁኔታ ሳይሆን በእውር ድንብስ ነበር።[23]

የመረብ ምላሽ (አሁኑ ኤርትራ) አስተዳዳሪ ባህር ንጉስ ይስሃቅ ከተደባለቀ በኋላ፣ አጠቃላዩ ሰራዊ ወደ ደቡብ በመነቀሳቀስ በ10ኛው ቀን ከግራኙ ጦር ፊት ለፊት አረፈ። በዚህ መሃል ክረምት ስለገባ በዝናቡ ምክንያት ደጋማ ለሶስተኛ ጊዜ ግራኝን ሊገጥመው ፈልጎ ግን ሳይችል ቀረ። በንግስት ሰብለ ወንጌል ጎትጓችነት ደጋማ በወፍላ፣ ከአሻንጌ ሃይቅ ፊት ለፊት፣ ከግራኝ ጦር ብዙም ሳይርቅ ክረምቱን አሳለፈ። [24] በዚህ ትይዩ ኢማሙ ደግሞ በ ዞብል ተራራወች ላይ ሰራዊቱን አስፈረ።[25]

ድል በጦር መሳሪያ ብዛት እንደሚወሰን የተገነዘበው ግራኝ ለእስላሙ አለም የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ። አረቦችም 2000 ጠመንጃወችና መድፎች እንዲሁም ከቱርክ 900 የተመረጡ ወታደሮች ተላኩለት። ባንጻሩ የፖርቹጋሎቹ ወታደሮች ብዛት በተለያዩ ግዴታወችና በጦርነት ላይ በደረሰው ሞት ምክንያት ከ400 ወደ 300 ዝቅ ብሎ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ ክረምት አልፎ በጋ ሲሆን በሃይል የተጠናከረው ግራኝ አህመድ በፖርቹጋሎቹ የጦር ቀጠና ላይ ጥቃት በማድረስ ቁጥራቸውን ወደ 140 አመናመነው። ክርስታቮ ደጋማም ቆስሎ 10 ከሚሆኑ ወታደሮቹ ጋር ተማረከ። በዚህ ጊዜ በሃይማኖቱ ከጸና እንደሚገደል እስላም ክሆነ ግን እንደማይገደል ተነግሮት ሃይማኖቴን አልቀይርም በማለቱ በተማረክበት ተገደለ። [26]

ከዚህ ጥቃት የተረፉትና የአጼ ገላውዲወስ ሰራዊት በመጨረሻ ተገናኝተው ሃይላቸውን በማጠናከር የካቲት 21፣ 1543 የወይና ደጋ ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ጥቃት አደረሱ። በዚህ ጦርነት 9000 የሚሆኑት የኢትዮጵያና ፖርቱጋል ሰራዊት 15000 የሚሆነውን የኢማሙን ሰራዊት አሸነፈ። የደጋማን ሞት ለመበቀል አልሞ የተነሳው አንድ የፖርቹጋል ወታደር በዚሁ ጦርነት ግራኝ አህመድን በጥይት ገደለው።

የግራኝ ሚስት፣ ባቲ ድል ወምበሬም ከተራረፉ የቱርክ ወታደሮች ጋር አምልጣ ሐረር ገባች። ተከታዮቿንም በማስተባበር የባሏን ሞት ለመበቀል የባሏን እህት ልጅ ኑር ኢብን ሙጃሂድን በማግባት ተነሳች። ኑር ኢብን ሙጃሂድም አጼ ገላውዲወስን በስተመጨረሻ እንደገደለው እና አንገቱን ቆርጦ ወደ ሐረር እንደላከው አንዳንድ የታሪክ ጸሓፊያን ይዘግባሉ::[27]

ማጣቀሻወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፉቱሑል ሐበሻ ሺሃቡዲን ኣረብ ፈቂህ

ሷሊሕ አስታጥቄ የፌስ ቡክ ገፅ

<https://www.facebook.com/sualihastatkehussen/>

 1. ^ Saheed A. Adejumobi, The History of Ethiopia, (Greenwood Press: 2006), p.178
 2. ^ Franz-Christoph Muth, "Ahmad b. Ibrahim al-Gazi" in Siegbert Herausgegeben von Uhlig, ed., Encyclopaedia Aethiopica: A-C (Wiesbaden:Harrassowitz Verlag, 2003), pp. 155.
 3. ^ Nikshoy C. Chatterji, Muddle of the Middle East, (Abhinav Publications: 1973), p.166
 4. ^ Charles Fraser Beckingham, George Wynn Brereton Huntingford, Manuel de Almeida, Bahrey, Some Records of Ethiopia 1593-1646: Being Extracts from the History of High Ethiopia or Abassia By Manoel De Almeida, Together with Bahrey's History of the Galla, (Hakluyt Society: 1954), p.105
 5. ^ Charles Pelham Groves, The Planting of Christianity in Africa, (Lutterworth Press: 1964), p.110
 6. ^ Richard Stephen Whiteway, Miguel de Castanhoso, João Bermudes, Gaspar Corrêa, The Portuguese expedition to Abyssinia in 1541-1543 as narrated by Castanhoso, (Kraus Reprint: 1967), p.xxxiii
 7. ^ William Leonard Langer, Geoffrey Bruun, Encyclopedia of World History: Ancient, Medieval, and Modern, Chronologically Arranged, (Houghton Mifflin Co.: 1948), p.624
 8. ^ Ewald Wagner, "`Adal" in Encyclopaedia Aethiopica: A-C, p.71
 9. ^ George Wynn Brereton Huntingford, The historical geography of Ethiopia from the first century AD to 1704, (Oxford University Press: 1989), p.135
 10. ^ The cross and the river: Ethiopia, Egypt, and the Nile - Page 204
 11. ^ George Wynn Brereton Huntingford, The historical geography of Ethiopia from the first century AD to 1704, (Oxford University Press: 1989), p.135
 12. ^ Getachew Metaferia - 2009 - "Ethiopia and the United States: History, Diplomacy, and Analysis" p.87
 13. ^ Walter Yust - "Encyclopaedia Britannica: a new survey of universal knowledge: Volume 1" p.76
 14. ^ Middleton, John (2008). "New encyclopedia of Africa". Basic Reference (NY, USA: Thomson/Gale) 1: 403. doi:10.1017/S0020743800063145. Retrieved 2012-04-27.
 15. ^ Annales d'Ethiopie">Lecoutre, Delphine (2006). "Annales d'Ethiopie". Basic Reference (Paris: de La Table Ronde) 1: 215. doi:10.1017/S0020743800063145. Retrieved 2012-09-05.
 16. ^ "A history of Ethiopia">Geofrey, C (1969). "A history of Ethiopia". Basic Reference (London: oxford university press) 1: 52. doi:10.1017/S0020743800063145. Retrieved 2012-09-05.
 17. ^ Laitin, David D.; Said S. Samatar (1987). Somalia: Nation in Search of a State. Boulder, Colorado: Westview Press. p. 12. ISBN 0865315558. http://books.google.com/books?id=DGFyAAAAMAAJ&dq=played+a+strong+role+in+the+Imam%27s+conquest+of+Abyssinia&q=principally+the&pgis=1. 
 18. ^ Basset, 1897 ገጽ 43 -44
 19. ^ The Ethiopians: a history By Richard Pankhurst.ገጽ 86
 20. ^ The battle is described in the Futuh, ገጽ 71-86.
 21. ^ The Ethiopians: a history By Richard Pankhurst.ገጽ 87፣ ሉዶልፍ 1684፣ ገጽ 221
 22. ^ Translated in Whiteway, The Portuguese Expedition, p. 41.
 23. ^ Whiteway, The Portuguese Expedition, p. 51.
 24. ^ Whiteway, The Portuguese Expedition, p. 53
 25. ^ G.W.B. Huntingford, The historical geography of Ethiopia from the first century AD to 1704, (Oxford University Press: 1989), p. 134
 26. ^ Described in terms worthy of a saint's life by Jerónimo Lobo, who based his account on the testimony of an eye witness. (The Itinerário of Jerónimo Lobo, translated by Donald M. Lockhart [London: Hakluyt Society, 1984], pp. 201-217)
 27. ^ Pankhurst, "Ethiopian Borderlands", p. 246.