Jump to content

ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ

ከውክፔዲያ
(ከዘርዓ ያዕቆብ የተዛወረ)

==

ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ1434 እስከ 1468 እ.ኤ.አ.
ቀዳሚ ዓምደ ኢየሱስ
ተከታይ በእደ ማርያም
ባለቤት ንግሥት እሌኒ
ሙሉ ስም ቆስጠንጥንዮስ (የዘውድ ስም)
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ቀዳማዊ ዳዊት
እናት ንግሥት ክብረ እግዚ
የተወለዱት 1399 እ.ኤ.አ. በትልቅ መንደር፣ ፈተገር ክ/ሀገር
የተቀበሩት ደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ክርስትና

==


የጥንቱ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት

አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስትክብረ እግዚ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው።

ኢሲራክ ዘሽሌ ገብረኪዳን ተጻፈ። ከኢልዮን የኢትዮጵያ ኅብረት

የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው።

ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። ንግስት እሌኒሀድያ ንጉስ ልጅ ስትሆን በህጻንነቱዋ የእስልምና ተከታይ የነበረች ቢሆንም በጋብቻው ወቅት ክርስቲያን ሆናለች።

በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤ/ክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቂቀ እስጢፋኖስ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ እየተባሉ በውሸት ታሪክ ስማቸው የጠፋ ስለ ትክክለኛ እምነት በብዙ ገድል ያለፉ ሰማዕታት ነበሩ ። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሊያሸንፏቸው ባለመቻላቸው ሊነገር በሚከብድ ቅጣት ኣንገታቸውን በመቁረጥ፡ኣባሎቻቸው መነኮሳይቱን በሰራዊታቸው በማስደፈር ኣፍንጫቸውን ምላሶቻቸውን እና ከንፈሮቻቸውን በመቁረጥ በኣራዊት እንዲበሉ በማድረግ ቀጥተዋቸዋል። በዚህም በዘመነ ንግስናቸው በፈጸሙት ኣረመኔናዊነት እየተዘከሩ ይኖራሉ ።

በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር።

አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20 በላይ መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው። ከነዚህም መካከል 1. መጽሐፈ ብርሐን 2. መጽሐፈ ሚላድ 3. መጽሐፈ ሥላሴ 4. መጽሐፈ ባሕርይ 5. ተዓቅቦ ምስጢር 6. ጦማረ ትስብእት 7. ስብሐተ ፍቁር 8. ክሂዶተ ሰይጣን 9. እግዚአብሔር ነግሠ 10. ድርሳነ መላእክት 11. ተአምረ ማርያም 12. ዜና አይሁድ 13. ጊዮርጊስ ወልደአሚድ 14. ተአምረ ማርያም ወኢየሱስ 15. ተአምረ ትስብኢት 16. ልፉፈ ጽድቅ 17. ትርጓሜ መላእክት 18. ተአምረ ጊዮርጊስ 19. ትርጓሜ ወንጌላት 20. መልክዓ ማርያም 21. መስተብቁዕ ዘመስቀል ይገኙበታል። እነዚህ መጽሐፎች ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ናቸው።

በተረፈ መባዓ ጽዮን የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጻዲቅ የኖረው በኒሁ ንጉስ ዘመን ነበር። ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ከኢትዮጵያ ነገሥታት 265ተኛ ነበሩ። [1]

  • (እንግሊዝኛ) David Buxon, The Abyssinians (New York: Praeger, 1970), pp. 48f
  • (እንግሊዝኛ) Richard K. P. Pankhurst, The Ethiopian Royal Chronicles (Addis Ababa: Oxford University Press, 1967), p. 32f.
  • (እንግሊዝኛ) Richard Pankhurst, The Ethiopians: A History (Oxford: Blackwell, 2001), p. 85.
  • Edward Ullendorff, however, attributes only the Mahsafa Berha and Mahsafa Milad.</ref>
  • www.ethioreaders.com

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]