ጥቅምት ፴
Appearance
ጥቅምት ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሁለተኛው ወር መጨረሻ፤ የዓመቱ ፷ኛ እና የመፀው ወቅት ፴፭ተኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፭ ቀናት ይቀራሉ።
ይሄ ዕለት በጀርመን አገር በ፲፰፻፵፩፤ ፲፱፻፲፩፤ ፲፱፻፲፮፤ ፲፱፻፴፩ እና ፲፱፻፹፩ ዓመተ ምሕረታት በተፈጸሙት ብሔራዊ ታሪኮች ምክንያት የአገሪቱ “የጦስ ቀን” (Schicksalstag (day of fate)) ይባላል።
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - የጀርመን ቄሳር ዳግማዊ ዊልሄልም ከዙፋናቸው እንደሚወርዱ በይፋ አሰታወቁ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - በጀርመን እና በአውስትሪያ አገሮች ናዚዎች የይሁዳውያን መቅደሳትና መደብሮችን በዝብዘው በእሳት አጋዩ። ይሄም ታሪካዊ ምዕራፍ “Kristallnacht” የመስተዋት መስበሪያ ምሽት በመባል ይታወቃል።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም - በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሕንድ ተወላጆች በማኅትማ ጋንዲ ስም ያቋቋሙት የማዋለጃ ሆስፒታል በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ። [1]
- ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ግዛቶችና በካናዳ ለአሥራ ሦስት ሰዐት ተኩል ያህል ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ስምንት መቶ ሺህ ሰዎች በኒው ዮርክ ውስጠ መሬት ባቡር ላይ ተደንቅረው አመሹ። ችግሩ በግምት የሃያ አምስት ሚሊዮን ሕዝቦችን ኑሮ አዛብቷል።
- ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. - በኮሙኒስታዊ የምሥራቅ ጀርመን ሪፑብሊክ የበርሊን ግንብ ፈረሰ። አገሪቷም ዙሪያ ድንበሮቿን በመክፈት ሕዝቦቿ ወደምዕራብ በነፃ እንዲጓዙ አመቻቸች።
- ፲፰፻፵፰ ዓ/ም - የሸዋ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም አርፈው በደብረ በግዕ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፴ ዓ.ም. - የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ራምሲ ማክዶናልድ
- ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. - የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኔቭል ቻምበርሌይን
- ፲፱፻፵፮ ዓ.ም. - የመጀመሪያው የሳውዲ አሬቢያ ንጉሥ አብዱላዚዝ አል ሳውድ
- ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአገራቸውን አርበኞች የመሩ እና ታዋቂው የፖለቲካ ሰው፣ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሻርል ደጎል በተወለዱ በ ሰባ ዘጠኝ ዓመታቸው አረፉ።
- ^ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ "ፍሬ ከናፍር። ዘ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ።" ፫ኛ መጽሐፍ (፲፱፻፶፯ ዓ/ም) ገጽ ፩ሺ ፬፻፷፮፮
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/big/1109.html
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/november/9/newsid_4275000/4275206.stm
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |