ማሀትማ ጋንዲ በመባል የሚታወቁት ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ ሕንድን ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛትነት ለማውጣት የተደረገውን ሰላማዊ ትግል መርተው ግብ ያገቡ መሪ ናቸው። እኚህ ታላቅ የሰላማዊ እንቅስቃሴ መሪ ጥር ፳፩ ቀን ፲፱፻፵ ዓ/ም በነፍሰ ገዳይ እጅ ተገደሉ።