ቶማስ ጄፈርሰን

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ቶማስ ጄፈርሰን

ቶማስ ጄፈርሰን (ሚያዝያ 7 ቀን 1735 ~ ሰኔ 28 ቀን 1818 ዓ.ም.) ከየካቲት 26 ቀን 1793 እስከ የካቲት 25 ቀን 1801 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ 3ኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኚያን ያቋቋሙት ጄፈርሰንም ነበሩ።

ቶማስ ጄፈርሰን ከአባቱ ከፒተር ጄፈርስን እና ከእናቱ ጄን ራንዶልፍ ተወለዱ። ቶማስ በአሜሪካ አብዮት ጊዜ በ1768 ዓ.ም. ከእንግሊዝ ንጉሥ የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ ጻፉ። በኋላ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመርከብ ሃያላት ወደ አልጀርስ ላኩ፣ ከናፖሌዎን ደግሞ ሰፊ መሬት በሚሲሲፒ ወንዝ አቅራቢያ (የሉዊዚያና አቅራቢያ የተባለው) ገዝተው ነበር። ይህ ድርጊት የአሜሪካ ስፋት በሁለት እጅ አስፋፋ።

ጄፈርሰን ከናፖሊዎን የገዙ 'የሉዊዚያና ክፍል' (ክፍት ቀይ)

ጥቅስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«እኛ እነዚህን እውነቶች ለራስ ግልጽ እንደ ሆኑ እንቆጠራለን፤ ሰዎች ሁሉ እኩል ሆነው ተፈጥረዋል፤ አንዳንድ የማይቋረጡ መብቶች በፈጣሪያቸው ተሰጥተዋል፤ ከነዚህም መካከል ሕይወት፣ አርነትና የደስታ ፍለጋ አሉ።» -- የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ