Jump to content

ታኅሣሥ ፲፫

ከውክፔዲያ

ታኅሣሥ ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፫ኛው እና የመፀው ወቅት ፸፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፷፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፷፪ ቀናት ይቀራሉ።


ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የጃንሆይ አጎት ደጃች ወልደ ሥላሴ ለመንግሥት ሥራ ደሴ ደርሰው ሲመለሱ አደጋ ተፈጥሮ ቀበቶ ሳያስሩ ቆመው ሲፎክሩ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ራሳቸውን በኃይል ስለመታቸው ከተሳፋሪዎቹ መካከል እሳቸው ብቻ በአደጋው ሞቱ። ስለኾነም በአይሮፕላን አደጋ በመሞት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እኒሁ የራስ መኮንን ወንድም ደጃች ወልደ ሥላሴ መሆናቸው ነው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በሁለት የአስመራ ቡና ቤቶች ላይ በተወረወሩ ተወርዋሪ ፈንጂዎች በተከሰተው አደጋ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ በተያያዘ የኤርትራ ነፃነት ግንባር አሰብ ወደብ አካባቢ የሰነዘረው ጥቃት ሦስት የጭነት መኪናዎችን አውድሟል።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በ፲፱፻፳፪ ዓ/ም የተደነገገውን ‘የኢትዮጵያ ዜግነት’ ሕግ በመሻር የሚተካው፤ ስለኢትዮጵያ ዜግነት የወጣው አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፰/፲፱፻፺፮ ከዚህ ዕለት ጀምሮ ሕግ ሆኖ እንደሚጸና በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታወጀ።
  • (እንግሊዝኛ) FLIGHT and AIRCRAFT ENGINEER - DECEMBER 27, 1929
  • {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974



የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ