አልጄሪያ
Appearance
(ከአልጀሪያ የተዛወረ)
الجمهورية الجزائرية الديمقراطية الشعبية |
||||
---|---|---|---|---|
|
||||
አልጄሪያ በአረንጓዴ ቀለም
|
||||
ዋና ከተማ | አልጂርዝ | |||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ዓረብኛ | |||
መንግሥት {{{ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
አብደላዚዝ ቡተፍሊካ አብደልማጂድ ተቡን |
|||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
2,381,740 (11ኛ) |
|||
ገንዘብ | የአልጄሪያ ዲናር | |||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||
የስልክ መግቢያ | +213 |
አልጄሪያ (አረብኛ፦ الجزائر አል ጃዝኤር; በርበርኛ፦ ድዜየር) በይፋ የአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከቆሳ ስፋት አኳያ በሜዲቴራንያን ባህር ዙሪያ ትልቋ ስትሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከሱዳን በኋላ ሁለተኛ ናት።
አልጄሪያ ከሰሜን ምሥራቅ በቱኒዚያ፣ ከምሥራቅ በሊቢያ፣ ከምዕራብ በሞሮኮ፣ ከደቡብ ምዕራብ በምዕራባዊ ሣህራ፣ ሞሪታኒያና ማሊ፣ ከደቡብ ምሥራቅ በኒጄር፣ ከሰሜን በሜዲቴራንያን ባህር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አልጂርዝ ሲሆን የ፳፻፫ ዓ.ም. ሕዝብ ብዛቷ ወደ 35.7 ሚሊዮን ይገመታል።
አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ ኦፔክ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ሀገር ናት።
የሀገሯ ስም የመጣው ከአልጂርዝ ከተማ ሲሆን በድሮ ጊዜ ከዛሬዎቹ ምዕራብ ቱኒዚያና ምሥራቅ ሞርኮ አብራ ኑሚዲያ ትባል ነበር።
በጥንት ጊዜ አልጄሪያ የኑሚዲያ መንግሥት ትባል የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቿ ደግሞ ኑሚዲያውያን ይባሉ ነበር። የኑሚዲያ መንግሥት ከካርታጎ፣ ሮማና ጥንታዊ ግሪክ ጋር ግንኙነት ነበራት። አካባቢው ለምለም እንደነበረ ሲነገር ኑሚዲያውያን ደግሞ ለኃይለኛ ፈረሰኛ ጦራቸው ይታወቁ ነበር።
|