ነሐሴ ፴
Appearance
(ከነሐሴ 30 የተዛወረ)
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፷ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፮ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፭ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፮፻፶፰ ዓ/ም - ለሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት የጋየው የሎንዶን “ታላቁ ቃጠሎ” በከተማዋ ፲ ሺህ ሕንጻዎችን ካወደመ በኋላ አቆመ።
- ፲፯፻፺፪ ዓ/ም - የፈረንሳይ ንጉሠ ነገሥት ናፖሌዎን የማልታን ደሴት በጦር ኃይል ግዴታ ለታላቋ ብሪታንያ ለቀቀ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኮንጎ ፕሬዚደንት ዮሴፍ ካዛቩቡ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባ ከሥልጣናቸው ሽረው በቁም እሥራት ላይ አዋሏቸው።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የግጥም ጠቢቡ ሌዎፖልድ ሴዳር ሴንግሆር በሴኔጋል የመጀመሪያ ፕሬዚደንት ሆእው ተመረጡ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቦክሰኛው ሞሀመድ አሊ (የቀድሞው ካሲየስ ክሌይ) በሮማው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር በመለስተኛ ክብደት ወርቅ ተሸለመ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - ሙኒክ ላይ በተካሄደው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር ላይ “ጥቁር መስከረም” ("Black September") የተባለ የፍልስጥኤም ሽብርተኛ ቡድን የእስራኤልን ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች በአፈና ከያዘ በኋላ አሥራ አንዱን ገደላቸው።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |