ጥቅምት ፳፭
Appearance
ጥቅምት ፳፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፭ኛ ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም - ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ በ እንጦጦ “መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም” ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዓ መንግሥት ተቀብተው የንጉሠ ነገሥት ዘውድ ጫኑ። [1]
- ፲፱፻ ዓ/ም - በነሐሴ ወር ፲፰፻፺፰ ዓ/ም ሥራውን የጀመረው በአዲስ አበባ እቴጌ ሆተል ተብሎ የተሠየመው የመጀመሪያው ሆቴል በዚህ ዕለት በአዲስ አበባ የነበሩ ዲፕሎማቶችና የውጭ አገር ዜጋዎች በተገኙበት በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ተመርቆ ተከፈተ። የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅም ፍሬደሪክ ሐል ነበር። በኋላ ግን አቶ ዘለቃ አጋርደው ተሾሙ።[2]
- ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - በሁንጋሪያ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በኢምሬ ናጊ መሪነት የተነሳውን ብሔራዊ የሕዝብ ዐመጽ ለመደምሰስ የሶቪዬት ሕብረት ወታደሮች የቡዳፔስትን ከተማ ወረሩ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. - የኢራን ሻህ ሬዛ ፓህላቪ በሕዝብ ፍንቀላ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ አብዮታዊ ተማሪዎች የአሜሪካን ኤምባሲ በኃይል ደምሥሠው ገብተው ዘጠና የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥራቸው ስር አዋሉ።
- ^ ኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ)፣ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል"፣ 1999
- ^ ጳውሎስ ኞኞ፣ "አጤ ምኒልክ"፣ገጽ ፫፻፳፱ ሦስተኛ ዕትም (፲፱፻፺፱ ዓ/ም)
http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/november/4
http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081101.html
http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081104.html
http://www.history.co.uk/this-day-in-history/November/04/also.html Archived ኖቬምበር 6, 2009 at the Wayback Machine