ኅዳር ፲፰

ከውክፔዲያ
(ከኅዳር 18 የተዛወረ)

ኅዳር ፲፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፰ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፰ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፯ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፴፬ ዓ/ም የፋሺስት ኢጣልያን የመጨረሻውን ይዞታ ጎንደርን ለማስለቀቅ አባቶቻችን አርበኞች ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በከተማዋ ዙሪያ ውጊያቸውን ጀመሩ። በዚሁ ዕለት ጄኔራል ናሲ ከነሠራዊቱ እጁን ሰጥቶ የአገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማፋሲለደስ ግንብ ላይ ተውለበለበ። በታሪክ መዝገብ የድል ቀን ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፻፴፫ ዓ/ም ቢባልም ኢትዮጵያ ከፋሺስቶች የተላቀቀችበት ዕለት ግን ኅዳር ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ/ም ነው።

፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በከፊል በናዚ ጀርመን ቁጥጥር ስር፤ በከፊል ደግሞ በጀርመን ደጋፊው የቪሺ አስተዳደር ስር የነበረችው የፈረንሳይ የባሕር ኃይል ቱሎን ወደብ ላይ የተሰበሰቡትን መርከቦቿን፣ በናዚዎች ቁጥጥር ስር እንዳይውሉ አሰመጧቸው።

፲፱፻፶፯ ዓ.ም. የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጃዋሃርላል ኔህሩ አሜሪካ እና የሶቪዬት ሕብረት የኑክሊዬር መሣሪያዎችን መፈተሻቸውን እንዲያቆሙና እንዲያውም ያላቸውን የኑክሊዬር መሣሪያዎች እንዲያጠፉ አቤቱታቸውን አቀረቡ።

፲፱፻፷፫ ዓ.ም. የካቶሊክ ጳጳስ ጳውሎስ ስድስተኛ ለጉብኝት ፊሊፒን አገር ሲደርሱ በማኒላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የቄስ ልብስ የለበሰና ጩቤ የያዘ የቦሊቪያ ተወላጅ፣ ጳጳሱን በመውጋት አቆሰላቸው።

፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በብሪታንያ በፖለቲካ የቀኙ ቡድን (Conservative party) መሪዋንና የአገሪቷን ጠቅላይ ሚኒስቴር ማርጋሬት ታቸርን ከሥልጣን ካወረደ በኋላ ተተኪ እንዲሆኑ ጆን ሜጀርን የቡድኑ መሪ አድርጎ መረጣቸው።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፰፻፷፯ ዓ.ም. የእስራኤል መንግሥት በግንቦት ፲፱፻፵፩ ሲመሠረት የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የሆኑት ዶክተር ኻይም ዋይዝማን

፲፰፻፹፯ ዓ.ም. መጀመሪያ የማትሱሺታ ኤለክትሪክ ፋብሪካ በኋላ ፓናሶኒክ የተባለውን ኩባንያ የመሠረቱት የጃፓን ዜጋ ኮኖሱኬ ማትሱሺታ[1]


፲፱፻፴፭ ዓ.ም. ጥቁር አሜሪካዊው በሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ “የጊታር ንጉሥ" የሚባለው ጂሚ ሄንድሪክስ

፲፱፻፶ ዓ.ም. ጋዜጠኛዋ እና የሕግ ባለሙያዋ የማቹ የፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ልጅ ካሮላይን ኬኔዲ

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2009-06-01. በ2009-11-10 የተወሰደ.