ሰንደቅ ዓላማ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
እስራኤል ሰንደቅ ዓላማ

ሰንደቅ ዓላማ በቋሚ ላይ እንዲውለበለብ የሚሰቀል ጨርቅ ነው። በድሮ ጊዜ መረጃ መለዋወጥ ዋነኛ ጥቅሙ ነበረ። በአሁኑ ጊዜ ግን የአንድን ሀገር ወይም ድርጅት ለመወከል ያገለግላል።

አቶ ከበደ ሚካኤል "ታሪክና ምሳሌ - ፩ኛ መጽሐፍ" በተባለው ድርሰታቸው ላይ፦ ሰንደቅ ዓላም የነጻነት ምልክት የአንድ ሕዝብ ማተብ፤ የኅብረት ማሰሪያ ጥብቅ ሐረግ ነው። «ተመልከት ዓላማህን፣ ተከተል አለቃህን።» ብለው አስፍረውታል።

«ሰንደቅ» የሚለው ቃል ከቱርክኛ «ሳንጃክ» ደረሰ። በኦቶማን ቱርክ ዘመን ይህም ከ«አላማ ሰንደቅ» በላይ «አስተዳደር ክልል» አመለከተ፣ ለምሳሌ የኖቪባዛር ሳንጃክ በዛሬው ሰርቢያ ዙሪያ እስካሁን «ሳንጃክ» ተብሏል።

እንዲሁም «ባንዲራ» የሚለው ቃል ከጣልኛ «ባንዲየራ» የአድዋ ጦርነት በኋላ ደረሰ። እሱና በሌሎች አውሮፓዊ ቋንቋዎች ተመሳሳይ ቃላት የመጡ ከቅድመ-ጀርማኒክ *ባንድ «ማሠርያ፣ ጥብጣብ» ነበር።

ሌሎች መጣጥፎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዓለም ባንዲራዎች