Jump to content

ታላቁ ፕዮትር

ከውክፔዲያ
የ13:12, 23 ሜይ 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ታላቁ ፕዮትር በ1709 ዓም

ታላቁ ፕዮትር (1664-1717 ዓም) ወይም 1 ፕዮትር1674 እስከ 1714 ዓም. ድረስ የመስኮብ ግዛት፣ ከ1714 እስከ 1717 ዓም ድረስ የሩስያ ግዛት ፃር (ንጉሥ) ነበሩ።

ከ1714 ዓም አስቀድሞ የንጉሡ ማዕረግ «ፃር» (ከሮማይስጥ ቄሣር) ሆኖ ነበር፤ በ1714 ዓም ፃሩ 1 ፕዮትር በይፋዊ ዐዋጅ ማዕረጉን ከ«ፃር» ወደ ሮማይስጡ «ኢምፔራቶር» (ንጉሰ ነገስት) ቀየረው። ከ1539 እስከ 1714 ዓም ድረስ ሀገሩ «የመስኮብ ግዛት» ወይንም «የሩስያ ግዛት» ሲባል፣ «ግዛት» የሚለው ሩስኛ ቃል በትክክል «ፃርነት»ን አመለከተ፤ ከ1714 ዓም ወዲኅ ግን «ግዛት» የሚለው ሩስኛ ቃል በትክክል «ኢምፔሪያ» (የንጉሠ ነገሥት መንግሥት) ሆነ።