አሚ-ዲታና
Appearance
አሚ-ዲታና ከ1596 እስከ 1559 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን 9ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን አቢ-ኤሹሕን ተከተለው።
ለአሚ-ዲታና ዘመን 37 የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እነዚህ የዓመት ስሞች ባጠቃላይ ስለ አረመኔ ጣኦታት የሚነካ ናቸው። 17ኛው ዓመት ወይም 1579 ዓክልበ. ያህል «የ<...> ምድር ሰው ያራሕ-አቢ የያዘበት ዓመት» ይባላል። ይህ ምናልባት በዓመፃ የተነሣ አለቃ ሊሆን ይችላል። በ37ኛው ዓመት የደር ከተማ ግድግዳ እንዳጠፋ ይዘገባል።
የአሚ-ዲታና ተከታይ ልጁ አሚ-ሳዱቃ ነበረ።
ቀዳሚው አቢ-ኤሹሕ |
የባቢሎን ንጉሥ 1596-1559 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ አሚ-ሳዱቃ |