Jump to content

አምባገነን

ከውክፔዲያ
የ02:08, 21 ሴፕቴምበር 2018 ዕትም (ከHgetnet (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

አምባገነንሥልጣናዊነት ሥርዓት ስር የሚመደብ የአገዛዝ ዓይነት ሲሆን፤ አንድ ግለሰብ ያለመንም የህግ ገደብ የፈለገውን የሚያስፈጽምበት፣ እና የፈለገውን ቢፈጽም ህግ እማይጠይቀው ፍጽም ሥልጣን ሲይዝ ማለት ነው። አምባገነኖች ወደ ሥልጣን አመጣጣቸው በህዝብ ተመርጠው፣ ሥልጣን በመንጠቅ፣ ወይንም በውጭ ሃይሎች ተፅዕኖ ሊሆን ይችላል። እንዲሁ፣ አምባገነኖች የግዴታ ዕኩይና ጨካኝ ላይሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ፣ ዕኩይ ተግባራትን ቢፈፅሙ የሚጠየቁበት መንገድ ስለሌለ፣ ከሞላ ጎደል የራስ ወዳድነት እና የኃይል ፍላጎታቸው በታሪክ ጭብጥ ውስጥ የጎላ ነው። በአሁኑ ዘመን፣ የአምባገነን ሥርዓት የኃይል ሚዛኑን ከተገዥዎች ለገዥ ስለሚያዳላ፣ ተቀባይነቱ እጅግ አንስተኛ ነው።