Jump to content

መንፈስ ቅዱስ

ከውክፔዲያ

መንፈስ ቅዱስክርስትና እምነት ከሥላሴ አንዱ ሲሆን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አእምሮ ያለዉ ማንነት ስሜት እና ፍቃድ ያለዉ እንደሆነ መፃፍ ቅዱስ ይናገራል መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው ያዝናል ኤፍ 4:30 መንፈስ ፈጣሪ ነው."የእግዛቤሬ መንፈስ ፈጠረኝ"እዮ 33:4

አብዛኛውን ጊዜ “መንፈስ” ተብለው የሚተረጎሙት ሩዋሕ የተባለው የዕብራይስጥ ቃልና ፕነቭማ የተባለው የግሪክኛ ቃል ብዙ ትርጉሞች አሏቸው። ሁሉም የሚያመለክቱት ለሰው ዓይን የማይታይንና በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝን አንድ ኃይል ነው። የዕብራይስጡና የግሪክኛው ቃላት የሚከተሉትን ነገሮች ለማመልከት ያገለግላሉ:- (1) ነፋስን፣ (2) በምድራዊ ፍጥረታት ውስጥ የሚሠራውን አንቀሳቃሽ የሕይወት ኃይል፣ (3) ከአንድ ሰው ምሳሌያዊ ልብ የሚወጣውንና አንዳንድ ነገሮችን በሆነ መንገድ እንዲሠራ ወይም እንዲናገር የሚያደርገውን አስገዳጅ ኃይል፣ (4) ከማይታይ ቦታ የሚመጡ መግለጫዎችን (5) ሕያው የሆኑ መንፈሳዊ አካላትን (6) አንቀሳቃሽ የሆነውን የአምላክ ኃይል ወይም መንፈስ ቅዱስ።

የተወሰነ አካል ወይስ ኃይል?

መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ መሰረት የራሱ የሆነ ህልውና ያለው እና በተቃራኒው የሌለው በሚመስል መልኩ ቀርቧል። መንፈስ ቅዱስ የራሱ ህልውና ያለው አካል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ሃሳብ ክርስቲያኖችን ለዘመናት ሲያጨቃጭቅ እንደነበረ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

መንፈስ ቅዱስ የተወሰነ አካል

በቀጥዮቹ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ (በግሪክኛ ጰራቅሊጦስ፣ “ረዳት” “አጽናኝ” “ጠበቃ” ) ‘የሚያስተምር’፣ ‘የሚመሰክር’፣ ‘የሚናገር’ እና ‘የሚሰማ’ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጿል።

  • የዮሐንስ ወንጌል 14፡15-16 "ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤"
  • የዮሐንስ ወንጌል 15፡26 "ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤"
  • የዮሐንስ ወንጌል 16፡13 "ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።"

በእነዚና በመሳሰሉት ጥቅሶች ላይ በመመስረት መንፈስ ቅዱስ የተወሰነ አካልና የራሱ የሆነ ስብዕና ያለው እንደሆነ አብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች ያምናሉ።

መንፈስ ቅዱስ የተወሰነ አካል አይደለም

የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት፦

  • የሉቃስ ወንጌል 1፡ 41 "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥"
  • የማቴዎስ ወንጌል 3፡11 "እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤"
  • የሐዋርያት ሥራ 10፡38 "እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤"

እነዚህ ጥቅሶች እንደሚያሳዩት መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የሚሞሉት ነገር፣ ልክ እንደ ውሃ የሚጠመቁበት፣ ወይም እንደ ዘይት የሚቀቡት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የጥንቱ የግሪክ ኮይነ ቋንቋ መሠረት የአንድ ነገር ፆታና ስብዕና ያለውና የሌለው መሆንን የሚያሳዩ የቃላት ክፍሎች አሉ። በዚህ መልኩ የኮይነ ቋንቋ አንድ ነገር ወይ ወንድ፣ ወይም ሴት፣ ወይም ግኡዝ ነገር ብሎ መክፈል ያስችላል። በዚህም መሰረት መንፈስ ቅዱስ እንደ "ወንድ" የተገለጸባቸውን ብዙ ቦታዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። ይሁንና በግኡዝ ፆታም የተገለጸባቸው ጥቂት የማይባሉ ጥቅሶች አሉ። (ለምሳሌ ያህል ዮሐንስ 14:17 ላይ "τὸ Πνεῦμα" ('ቶ ፕኒውማ' ወይም 'መንፈሱ') የተገለጸው በግኡዝ ፆታ ነው።)

አንዳንድ ምንጮችስ ምን ይላሉ?

ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ እንዲህ ይላል:- “በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ጥቅሶች የአምላክን መንፈስ የሚገልጹት የተወሰነ አካል እንደሆነ ሳይሆን ረቂቅ ነገር እንደሆነ አድርገው ነው። መንፈስና የአምላክ ኃይል ተመሳሳይ እንደሆኑ ተደርጎ መገለጹ ይህንን ያስረዳል።” (1967፣ ጥራዝ 13፣ ገጽ 575)

ያው መጽሐፍ በተጨማሪ እንዲህ ሲል ዘግቧል:- “አፖሎጂስቶች [በሁለተኛው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት በግሪክኛ ቋንቋ ይጽፉ የነበሩ ክርስቲያን ጸሐፊዎች] ስለ መንፈስ የተናገሩት በጣም ያዝ እያደረጋቸው፣ ወደፊት የሚሆነውን በመጠበቅ፣ የተወሰነ አካል እንደሌለው አድርገው ነው።”—ጥራዝ 14፣ ገጽ 296

ማጠቃለያ

በዚህም ምክንያት በመንፈስ ቅዱስ ምንነትና ማንነት ዙሪያ የክርስትና ኃይማኖቶች ለሁለት እንደተከፈሉ እንመለከታለን።